መዝሙር 117
ጥሩነት
-
1. ይሖዋ ሆይ፣ ደግ አምላክ ነህ።
ብዙ ነው በረከትህ።
ወደር የለው ጥሩነትህ፤
ታማኝ አምላካችን ነህ።
ይገባናል ለማንለው
ሞገስህ ’ናመስግንህ።
አምልኳችን ይገባሃል፤
በደስታ ’ናገልግልህ።
-
2. የሕዝቦችህ መልካም ምግባር፣
ወንጌሉን መስበካቸው፣
ያሳያል ጥሩነትህን
እንደሆንክ አምላካቸው።
በደግነት አስተማርከን፤
እረኞችን ሾምክልን።
መንፈስህን ’ባክህ ስጠን፤
እኛም ጥሩ እንድንሆን።
-
3. ሳናዳላ ለሁሉም ሰው
ስናሳይ ጥሩነትን፣
ወንድሞችን ስንረዳቸው
ስጠን በረከትህን።
በቤተሰብ፣ በጉባኤ፣
ባገልግሎት ላይ ስንሆን
በመንፈስህ በመታገዝ
እናሳይ ጥሩነትን።
(በተጨማሪም መዝ. 103:10ን፣ ማር. 10:18ን፣ ገላ. 5:22ን እና ኤፌ. 5:9ን ተመልከት።)