መዝሙር 116
ደግነት ያለው ኃይል
-
1. አምላክ ሆይ፣ ከልብ እናወድስህ፤
ስለ ባሕርያትህ።
ታላቅ ቢሆንም ኃይልህ፣ ጥበብህ
ወደር የለው ደግነትህ።
-
2. ሸክም ከብዷቸው የደከሙትን
ልጅህ ጋብዟቸዋል።
ቀንበሩ ልዝብ፣ ሸክሙ ቀላል ነው፤
ማጽናኛ ከሱ ይገኛል።
-
3. አምላክንና ’የሱስን መምሰል፣
ፍላጎታችን ነው።
አዛኞችና ደጎች እንሁን፤
ደግነት ትልቅ ኃይል አለው።
(በተጨማሪም ሚክ. 6:8ን፣ ማቴ. 11:28-30ን፣ ቆላ. 3:12ን እና 1 ጴጥ. 2:3ን ተመልከት።)