መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 2014 | ወደ አምላክ መቅረብ ትችላለህ
አምላክ የማይቀረብ እንደሆነ ይሰማሃል? የአምላክ ወዳጅ መሆን የሚቻል ይመስልሃል?
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
የአምላክን ስም ታውቀዋለህ? በስሙስ ትጠቀማለህ?
አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ “እኔ ይሖዋ ነኝ። ስሜ ይህ ነው” በማለት ራሱን አስተዋውቆሃል።
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
ከአምላክ ጋር ትነጋገራለህ?
በጸሎት አማካኝነት ለአምላክ ሐሳባችንን መንገር እንችላለን፤ ይሁንና እሱ ሲናገር ማዳመጥ የምንችለው እንዴት ነው?
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
አምላክ የሚጠይቅህን ነገር ታደርጋለህ?
አምላክን መታዘዝ አስፈላጊ ነገር ነው፤ ይሁንና የእሱ ወዳጆች መሆን ከፈለግን ማድረግ ያለብን ሌላም ነገር አለ።
ቲምጋድ—የተቀበረው ጥንታዊ ከተማ ሚስጥር ተገለጠ
የጥንቶቹ ሮማውያን በሰሜን አፍሪካ ከሚኖሩ ዘላን ሕዝቦች ጋር ሰላም ለመፍጠር ሲሉ አንድ ስውር ዘዴ ተጠቅመዋል።
“ጥልቅ ማስተዋል ሰውን ቶሎ እንዳይቆጣ ያደርገዋል”
የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ዳዊት በሕይወቱ ውስጥ ያጋጠመው አንድ ክስተት፣ የሚያናድድ ወይም የሚያስቆጣ ነገር ቢያጋጥምህ ስሜትህን መቆጣጠር የምትችለው እንዴት እንደሆነ ያስተምርሃል።
ገንዘብ መበደር ይኖርብኛል?
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኙት ምክሮች ይህን ለመወሰን ይረዱሃል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለልጆቻችሁ መጽሐፍ ቅዱስን በጥሩ መንገድ ማስተማር የምትችሉት እንዴት ነው?
በተጨማሪም . . .
አምላክ፣ የራሱ ማንነት የሌለው ኃይል ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ሁሉንም ነገሮች እንደፈጠረ ይገልጻል፤ ይሁንና ስለ እኛስ በግል ያስባል?