ቅዱስ ለሆኑ ነገሮች አድናቆት ይኑርህ!
ለታዳጊ ወጣቶች
ቅዱስ ለሆኑ ነገሮች አድናቆት ይኑርህ!
መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።
ዋነኞቹ ባለ ታሪኮች፦ ይስሐቅ፣ ርብቃ፣ ያዕቆብ እና ዔሳው
ታሪኩ በአጭሩ፦ ዔሳው ብኩርናውን ለመንታ ወንድሙ ለያዕቆብ ሸጠለት።
1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ዘፍጥረት 25:20-34ን አንብብ።
ያዕቆብና ዔሳው ገና በእናታቸው ሆድ ውስጥ እያሉ እንኳ ምን ዓይነት ጠባይ ያሳዩ ነበር?
․․․․․
ያዕቆብንና ዔሳውን በአእምሮህ ስትስላቸው ወጣት ሳሉ እንዴት ዓይነት ቁመና የነበራቸው ይመስልሃል?
․․․․․
ከቁጥር 30 እስከ 33 ላይ በሚገኘው ዘገባ መሠረት ያዕቆብና ዔሳው ሲነጋገሩ ምን ዓይነት ስሜት የነበራቸው ይመስልሃል?
․․․․․
ጥልቅ ምርምር አድርግ።
ምርምር ማድረግ የምትችልባቸውን መሣሪያዎች በመጠቀም የበኩር ልጅ ምን መብቶች እንደነበሩት ለማወቅ ሞክር። እነዚህ መብቶች ጠቃሚ ነበሩ የምንለው ለምንድን ነው? እነዚህን መብቶች በአንድ ሳህን ምስር ወጥ መሸጥስ ምን ጥቅም ነበረው?
․․․․․
2 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ዘፍጥረት 27:1-10, 30-38ን አንብብ።
ዔሳው በብኩርና የሚገኘውን በረከት ወንድሙ እንደወሰደበት ባወቀ ጊዜ እንዴት ባለ የድምፅ ቃና የተናገረ ይመስልሃል?
․․․․․
ጥልቅ ምርምር አድርግ።
ርብቃ፣ ያዕቆብ በረከት እንዲያገኝ ስትል ሁኔታዎችን ማቀነባበሯ ስህተት ነበር? ያዕቆብስ ከእሷ ጋር መተባበሩ ትክክል ነበር? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው? (ፍንጭ፦ ዘፍጥረት 25:23, 33ን ተመልከት።)
․․․․․
3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለሰፈረው ሐሳብ ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦
ጊዜያዊ ደስታ ለማግኘት ተብሎ የሚደረግ ውሳኔ ስለሚያስከትለው ዘላቂ መዘዝ።
․․․․․
ልትሠራበት የሚገባ ተጨማሪ ነገር።
በአደራ የተሰጡህ ቅዱስ ነገሮች ምንድን ናቸው?
․․․․․
ቅዱስ ለሆኑ ነገሮች አድናቆት እንዳለህ ማሳየት የምትችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
․․․․․
4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ይበልጥ ትምህርት ያገኘህበት ሐሳብ የትኛው ነው? ለምን እንዲህ አልክ?
․․․․․
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።