መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ነሐሴ 2013

ይህ እትም የአምላክን ሥራ ስናከናውን ቅዱስ ሆነን መኖርና በእሱ አገልግሎት ጠቃሚ ድርሻ ማበርከት፣ በአምላክ ላይ ከመቆጣት መቆጠብ እንዲሁም ተስፋ መቁረጥን ማሸነፍ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

ተቀድሳችኋል

ቅዱስ ሆነን ለመቀጠልና ምንጊዜም በይሖዋ አገልግሎት ጠቃሚ ድርሻ ለማበርከት ሊረዱን የሚችሉ አራት ነገሮችን እንመርምር።

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ክርስቲያን ወላጆች በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ሲገኙ ከተወገደ ልጃቸው ጋር መቀመጣቸው ተገቢ ነው?

የሕይወት ታሪክ

ይሖዋ ‘ሸክሜን በየዕለቱ ይሸከምልኛል’

በናሚቢያ የተወለደች አንዲት እህት ከባድ የጤና ችግር ቢኖርባትም ከ20 ለሚበልጡ ዓመታት ደስተኛ ሆና በአቅኚነት እንድታገለግል የረዳት ምንድን ነው?

ፈጽሞ ‘በይሖዋ ላይ አትቆጡ’

አንዳንዶች በልባቸው በአምላክ ላይ ተቆጥተዋል። ለችግራቸው ተጠያቂ የሚያደርጉት እሱን ነው። እንዲህ ካለው ወጥመድ መራቅ የምንችለው እንዴት ነው?

ወላጆች—ልጆቻችሁን ከጨቅላነታቸው ጀምሮ አሠልጥኗቸው

እንዲህ ዓይነቱ ሥልጠና መጀመር ያለበት መቼ ነው? ምን ነገሮችንስ ሊያጠቃልል ይገባል?

አንዳችን ለሌላው ትኩረት እንስጥ፤ እርስ በርስም እንበረታታ

ችግሮች ቢያጋጥሙንም እንኳ አምላክን በታማኝነት ማገልገላችንን ለመቀጠል አንዳችን ሌላውን ማበረታታት የምንችለው እንዴት ነው?

ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለባችሁ አስቡ

ሰይጣን በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንድናገኝ አይፈልግም። ከይሖዋ ጋር ያለንን ወዳጅነት ለመጠበቅ ምን ማድረግ እንችላለን?

ኤልሳዕ የእሳት ሠረገሎችን አይቷል—አንተስ ይታዩሃል?

ኤልሳዕ በይሖዋ ሙሉ በሙሉ ይተማመን ነበር። እሱ ከተወው ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን?

ከታሪክ ማኅደራችን

ንጉሡ እጅግ ተደሰቱ!

የስዋዚላንድ ንጉሥ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን በአድናቆት የተቀበሉት እንዴት እንደሆነ አንብብ።