የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
ሕይወት እንዴት ጀመረ?
የሚከተለውን ዓረፍተ ነገር አሟላ፦
ሕይወት የተገኘው በ․․․․․ ነው።
-
ዝግመተ ለውጥ
-
ፍጥረት
አንዳንዶች፣ ሳይንሳዊ አስተሳሰብ ያለው ሰው ከላይ ለቀረበው ጥያቄ “ዝግመተ ለውጥ” የሚለውን እንደሚመርጥ፣ ሃይማኖተኛ የሆነ ሰው ደግሞ “ፍጥረት” ብሎ እንደሚመልስ ያስቡ ይሆናል።
ይህ ግን ሁልጊዜ ትክክል አይደለም።
እንደ እውነቱ ከሆነ በርካታ ሳይንቲስቶችን ጨምሮ ብዙ የተማሩ ሰዎች የዚህን ጽንሰ ሐሳብ ትክክለኛነት ይጠራጠራሉ።
ኮሌጅ ሳሉ ስለ ዝግመተ ለውጥ የተማሩትንና የነፍሳት ጥናት ፕሮፌሰር የሆኑትን ዠራርድን እንደ ምሳሌ እንውሰድ። “ፈተና በምፈተንበት ጊዜ ፕሮፌሰሮቹ የሚፈልጉትን መልስ እሰጥ ነበር፤ እኔ ግን አላምንበትም” ብለዋል።
ለመሆኑ ሳይንሳዊ አመለካከት ያላቸው ሰዎችም ሳይቀር ሕይወት የተገኘው በዝግመተ ለውጥ ነው ብሎ መቀበል የሚከብዳቸው ለምንድን ነው? የዚህን መልስ ለማግኘት ብዙ ተመራማሪዎችን ግራ ያጋቡ ሁለት ጥያቄዎችን እንመልከት፦ (1) ሕይወት የጀመረው እንዴት ነው? (2) ሕይወት ያላቸው ነገሮች ዛሬ ያላቸውን መልክ ሊይዙ የቻሉት እንዴት ነው?