መጽሐፍ ቅዱስ የያዘው መልእክት ምን እንደሆነ ታውቃለህ?
መጽሐፍ ቅዱስ የያዘው መልእክት ምን እንደሆነ ታውቃለህ?
● በታሪክ ዘመናት ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል በስፋት የተሰራጨ ሌላ መጽሐፍ የለም። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘው መልእክት በየትኛውም ባሕል ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች መጽናኛና ተስፋ ሰጥቷቸዋል፤ መጽሐፉ የሚሰጠው ምክርም በዕለታዊ ሕይወታቸው ጠቅሟቸዋል። ሆኖም በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ያላቸው እውቀት ውስን ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው? የተሰኘው የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት አጠር ባለ መንገድ የያዘና ማራኪ ሥዕሎች ያሉት ብሮሹር ይህን መጽሐፍ ለመረዳት ያስችልሃል። የመጀመሪያዎቹ ሁለት ክፍሎች፣ አምላክ መጀመሪያ ለሰዎች ገነትን ሰጥቶ እንደነበረና ሰዎች በዚያ የመኖር መብታቸውን እንዴት እንዳጡ ይገልጻሉ። ቀጣዮቹ ክፍሎች ደግሞ ፈጣሪ ባቋቋመው መንግሥት አማካኝነት ምድርን እንደገና ገነት የማድረግ ዓላማ እንዳለው ያብራራሉ፤ ይህ መንግሥት በኢየሱስ ክርስቶስ የሚመራ ሰማያዊ መስተዳደር ነው።
ቀጥሎ ያሉት ክፍሎች ደግሞ ኢየሱስ ስላከናወነው አገልግሎት፣ ስለፈጸማቸው ተአምራት እንዲሁም ስለ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ይናገራሉ። ከዚያ በኋላ ያሉት ክፍሎች ደፋር ስለነበሩት የመጀመሪያዎቹ የኢየሱስ ተከታዮችና በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ስለጻፏቸው መጻሕፍት ይገልጻሉ፤ እነዚህ መጻሕፍት በአሁኑ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሆነዋል።
ሃያ ስድስት ክፍሎች ያሉት ይህ ብሮሹር የሚደመደመው “ምድር ገነት ትሆናለች!” በሚል ርዕስ መሆኑ ትኩረት የሚስብ ነው። በሚያምሩ ቀለማት የተዘጋጀው 31ኛው ገጽ “የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት—አጠቃላይ ይዘት” የሚል ርዕስ አለው። በዚህ ርዕስ ሥር አምላክ ለሰው ልጆች ባለው ዓላማ ፍጻሜ ረገድ የተከናወኑ ሰባት ወሳኝ ነጥቦች ጠቅለል ተደርገው ቀርበዋል።
ይህን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ እዚህ ላይ የሚታየውን ብሮሹር ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።