ቤተሰብ የሚወያይበት
ቤተሰብ የሚወያይበት
የሁለቱ ሥዕሎች ልዩነት ምንድን ነው?
በሥዕል ሀ እና በሥዕል ለ መካከል ያሉትን ሦስት ልዩነቶች መናገር ትችላለህ? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሎቹ የተሟሉ እንዲሆኑ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።
ፍንጭ፦ ዘፀአት 28:9-12, 33, 36, 37ን አንብብ።
1. ․․․․․
2. ․․․․․
3. ․․․․․
4. ትክክለኛው ሥዕል የትኛው ነው? በቀኝ ያለው ነው ወይስ በግራ?
․․․․․
ለውይይት፦
“ቅዱስ” ማለት ምን ማለት ነው? የይሖዋ አገልጋዮች ቅዱስ መሆን ያለባቸው ለምንድን ነው? ቅዱስ ለመሆን ጥረት እያደረግህ መሆንህን ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?
ፍንጭ፦ 2 ቆሮንቶስ 7:1ን አንብብ።
ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦
እያንዳንዱ የቤተሰባችሁ አባል በጥንት እስራኤላውያን ዘመን አንድ ሊቀ ካህናት ምን የሥራ ድርሻ እንደነበረው ለማወቅ ምርምር ያድርግ። ከዚያም አንድ ላይ ተሰብሰቡና ምን እንዳገኛችሁ ተነጋገሩ። ለምሳሌ ያህል፣ ሊቀ ካህናት ካሉበት ኃላፊነቶች አንዳንዶቹ ምን ነበሩ?
ፍንጭ፦ ዘሌዋውያን 9:7ን እና ዘዳግም 17:9-11ን አንብብ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁሉ የተሻለ ሊቀ ካህናት መሆኑን ያስመሠከረው እንዴት ነው?
ፍንጭ፦ ዕብራውያን 4:14-16ን፤ 7:26-28ን እና 9:11-14ን አንብብ።
ካርድ በመሰብሰብ መማር
ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው
የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 3 ሩት
ጥያቄ
ሀ. ሩት ለኑኃሚን የተናገረችውን ዓረፍተ ነገር አሟላ፦ “ሕዝብሽ . . .”
ለ. የታመሙትንና አረጋውያንን ለሚንከባከቡ ሰዎች ሩት ጥሩ ምሳሌ የሆነችው እንዴት ነው?
ሐ. ክፍት ቦታዎቹን ሙላ። ሩት ․․․․․ን አግብታ የ ․․․․․ እና ․․․․․ቅድመ አያት ሆናለች።
[ሰንጠረዥ]
4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ
ሩት የኖረችበት ዘመን በ1200ዎቹ ዓ.ዓ. ገደማ
1 ዓ.ም.
98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ
[ካርታ]
ከሞዓብ ወደ ቤተልሔም ተጓዘች
ሞዓብ
ቤተልሔም
ሩት
አጭር የሕይወት ታሪክ፦
ኑኃሚን የተባለችውን በዕድሜ የገፋች አማቷን የረዳች ታማኝ ሞዓባዊት መበለት። ሩት ለኑኃሚን የነበራት ጽኑ ፍቅርና ይሖዋን ለማምለክ ያደረገችው ቁርጥ ውሳኔ የትውልድ አገሯን ትታ ወደ ቤተልሔም እንድትሄድ አነሳስቷታል። ሰዎች ኑኃሚንን ‘ምራትሽ ከሰባት ወንዶች ልጆች ትበልጥብሻለች’ ብለዋታል።—ሩት 4:14, 15
መልስ
ሀ. “. . . ሕዝቤ፤ አምላክሽ አምላኬ ይሆናል።”—ሩት 1:16
ለ. ሩት የራስን ጥቅም የመሠዋትና የታታሪነት መንፈስ አሳይታለች።—ሩት 2:7, 10-12, 17፤ 3:11
ሐ. ቦዔዝ፣ ንጉሥ ዳዊት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ።—ማቴዎስ 1:5, 6, 16
ሕዝቦችና አገሮች
5. ሻኤ እባላለሁ። የምኖረው ለአውሮፓ አህጉር ቅርብ በሆነችው በብሪታንያ ነው። በብሪታንያ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 13,300, 133,000 ወይስ 333,000?
6. የምኖርበትን አገር በሚጠቁመው ፊደል ላይ አክብብ። ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከብሪታንያ ምን ያህል የሚርቅ ይመስልሃል?
ሀ
ለ
ሐ
መ
ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።
● በገጽ 30 እና 31 ላይ የቀረቡት ጥያቄዎች መልስ በገጽ 7 ላይ ይገኛል
በገጽ 30 እና 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
1. በጥምጥሙ ላይ ያሉት ቃላት።
2. ትከሻው ላይ ያሉት መረግዶች።
3. በዘርፉ ላይ ያሉት ሻኩራዎች።
4. በስተግራ ያለው።
5. 133,000
6. ለ።