መልስህ ምንድን ነው?
መልስህ ምንድን ነው?
ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?
የሐዋርያት ሥራ 10:9-48ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በጥቅሱ ውስጥ ከተገለጹት ነገሮች መካከል የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ፤ እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን የጎደሉትን ነገሮች ቦታ ቦታቸው ላይ ሳል።
1. ․․․․․
2. ․․․․․
3. ․․․․․
ለውይይት፦
ይሖዋ ጴጥሮስ እንዲያገኝ የፈለገው ትምህርት ምን ይመስልሃል?
ፍንጭ፦ የሐዋርያት ሥራ 10:28, 34, 35ን አንብብ።
ከአንተ የተለየ ዘር ወይም ባሕል ካላቸው ሰዎች ጋር ስትገናኝ ከጴጥሮስ ትምህርት እንዳገኘህ በሚያሳይ መንገድ ልትይዛቸው የምትችለው እንዴት ነው?
ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።
ከዚህ እትም
የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።
ጽ 9 ሰዎች መቼም ቢሆን ማወቅ የማይችሉት ነገር ምንድን ነው? መክብብ 3:․․․
ገጽ 10 አምላክ ምድርን የሰጠው ለእነማን ነው? መዝሙር 115:․․․
ገጽ 13 ደስተኞች እንድንሆን ምን ነገር ማወቅ አለብን? ማቴዎስ 5:․․․
ገጽ 19 ዕቅድ የሚፋለሰው መቼ ነው? ምሳሌ 15:․․․
ስለ መስፍኑ ሳምሶን ምን የምታውቀው ነገር አለ?
ከመሳፍንት 13:1 እስከ 16:31ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ።
4. ․․․․․
ከየትኛው ነገድ ነበር?
5. ․․․․․
እስራኤልን ያዳነው ከየትኛው ሕዝብ ነበር?
6. ․․․․․
እውነት ወይስ ሐሰት? ሳምሶን የኖረው ከነቢዩ ሳሙኤል በኋላ ነው።
ለውይይት፦
ሳምሶን በጣም ኃይለኛ የነበረው ለምንድን ነው?
ፍንጭ፦ ዕብራውያን 11:32-34ን አንብብ።
ይበልጥ ደስ የሚልህ የትኛው የሳምሶን ታሪክ ነው? እንዲህ ብለህ የመለስከውስ ለምንድን ነው?
▪ መልሱ በገጽ 22 ላይ ይገኛል
በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች
1. አራት እግር ያላቸው ፍጥረታት የሉም።
2. በደረታቸው የሚሳቡ ፍጥረታት የሉም።
3. ወፎች የሉም።
4. ዳን።—መሳፍንት 13:2-5
5. ፍልስጥኤማውያን።—መሳፍንት 13:1
6. ሐሰት።