ከማንኛውም መጫወቻ ይበልጥ የሚወደድ
ከማንኛውም መጫወቻ ይበልጥ የሚወደድ
ትንንሽ ልጆች አንድን መጽሐፍ ከመጫወቻ አስበልጠው ሊወዱ ይችላሉ? አዎን፣ ወላጆች ልጆቻቸው ገና ሕፃናት ሳሉ ጀምሮ የተለያዩ መጻሕፍትን የሚያነቡላቸው ከሆነ አስበልጠው ሊወዱ ይችላሉ። ካሊፎርኒያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚኖሩ መብራህቱ እና አንጄላ የተባሉ አንድ ባልና ሚስት ሴት ልጃቸው ከተወለደችበት ጊዜ አንስቶ ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ ያነቡላት ነበር።
የሕፃኗ ወላጆች ይህን በሚመለከት እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል:- “በዚህም ምክንያት ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ የተባለውን መጽሐፍ እየወደደችው መጣች። ገና የአንድ ዓመት ሕፃን ሳለች የኢየሱስ መጽሐፍ ብላ የምትጠራውን ይህን መጽሐፍ እንድናነብላት አፍ አውጥታ መጠየቅ ጀመረች። ጁሊያና አሁን የሦስት ዓመት ልጅ ስትሆን በየዕለቱ ከእናቷ ወይም ከአባቷ ጋር ይህን መጽሐፍ በማጥናት የምታሳልፈውን አስደሳች ጊዜ በጉጉት ትጠባበቃለች። ልጃችን ከማንኛውም መጫወቻ ይበልጥ ይህን መጽሐፍ ትወደዋለች ብንል ማጋነን አይሆንብንም። ሥዕሎቹና ምሳሌዎቹ በራሳቸው ጠቃሚ የማስተማሪያ መሣሪያዎች ናቸው። እኛ ወላጆችም እንኳ ብዙ ተምረናል።”
እርስዎም ውብ ሥዕሎችን የያዘውና ከዚህ መጽሔት ጋር ተመሳሳይ መጠን ያለው ይህ ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ እንዲላክልዎት መጠየቅ ይችላሉ። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።