“የመጽሔቶቻችሁ ሱሰኛ ሆኛለሁ”
“የመጽሔቶቻችሁ ሱሰኛ ሆኛለሁ”
በቅርቡ ጀርመን የሚገኘው የመጠበቂያ ግንብ ማኀበር ቅርንጫፍ ቢሮ የደረሰው ደብዳቤ በከፊል እንዲህ ይነበባል:-
“የመጽሔቶቻችሁ ሱሰኛ መሆኔን ሳልደብቅ ልንገራችሁ። በየዓመቱ ተመሳሳይ ነገር ያጋጥመኛል። ለእረፍት ወደ አንድ የባሕር ዳርቻ ከመሄዴ በፊት በቅርቡ የወጡትን ሁለት የንቁ! መጽሔት እትሞች እዚያ ሆኜ ለማንበብ ቁርጥ ውሳኔ አደርጋለሁ!
“ይሁን እንጂ መጽሔቶቹ ልክ እጄ እንደገቡ ችግሩ ይጀምራል። እስቲ ማውጫውን ብቻ ልመልከት እልና ማገላበጥ ስጀምር ዓይኔ የሕይወት ታሪክ የሚለው ላይ ያርፋል። ቆይ እስቲ ለቅምሻ ያህል ይህንን ብቻ አንብቤ አቆማለሁ ብዬ እጀምራለሁ። ወይኔ የሚቀጥለው ርዕስ ደግሞ ደስ የሚል ይመስላል። አሁንስ በቃ! መጽሔቶቹን እኮ ለእረፍት ጊዜዬ እፈልጋቸዋለሁ እልና ከዚያ ደግሞ እሺ አንድ የመጨረሻ እላለሁ። “ከዓለም አካባቢ” ደግሞ ሁልጊዜ አዳዲስ ሐሳቦች የያዘ ነው! በመጨረሻ ባሕር ዳርቻው ስደርስ ምን እንደሚሆን መገመት ትችላላችሁ። ሁሉንም አንብቤ ስለጨረስኩ አንድም የሚነበብ ርዕስ አይቀረኝም።”
ንቁ! መጽሔት በእያንዳንዱ እትም 20,300,000 የሚደርስ ቅጂ በ82 ቋንቋዎች መታተሙ ምን ያህል ተፈላጊ እንደሆነ ያሳያል። አንባቢዎች መጽሔቱ ላይ የሚወጡትን አዎንታዊ ሐሳቦች ይወዷቸዋል። “ንቁ! የሚታተምበት ምክንያት” በሚለው ክፍል ሥር እንደተብራራው “ይህ መጽሔት አሁን ያለውን ክፉና ዓመፀኛ ሥርዓት የሚተካ ሰላም የሰፈነበትና አስተማማኝ አዲስ ዓለም እንደሚመጣ ፈጣሪ በሰጠው ተስፋ ላይ ሰዎች ያላቸውን እምነት እንዲያሳድጉ ያደርጋል።”
ይሁን እንጂ ብዙዎች “አምላክ ይህን ለሚያህል ጊዜ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?” በማለት ይጠይቃሉ። ይህ ጥያቄ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? በሚለው ብሮሹር ላይ መልስ አግኝቷል። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህ ብሮሹር እንዲላክልዎ መጠየቅ ይችላሉ።
□ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።