አንተም ጥበብ ማግኘት ትችላለህ
“ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው።” (2 ጢሞቴዎስ 3:16) ጥቅሱ ላይ “በአምላክ መንፈስ መሪነት” ሲል ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሐሳቡን በመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች አእምሮ ውስጥ እንዳስቀመጠ መናገሩ ነው።
አምላክ እሱ የሚሰጠውን ጥበብ በማወቅ ጥቅም እንድታገኝ ጋብዞሃል
“የሚጠቅምህን ነገር የማስተምርህ፣ ልትሄድበትም በሚገባህ መንገድ የምመራህ እኔ ይሖዋ . . . ነኝ። ትእዛዛቴን ብትሰማ ምንኛ መልካም ነው! እንዲህ ብታደርግ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ ይሆናል።”—ኢሳይያስ 48:17, 18
እነዚህን ቃላት አምላክ ለአንተ በግልህ ያቀረበልህ ግብዣ አድርገህ ተመልከታቸው። አምላክ ውስጣዊ ሰላም እንድታገኝና ሁልጊዜ ደስተኛ እንድትሆን ይፈልጋል፤ ሰላምና ደስታ እንድታገኝ ሊረዳህም ይችላል።
አምላክ የሚሰጠውን ጥበብ አንተም መማር ትችላለህ
“ምሥራቹ ለብሔራት ሁሉ መሰበክ አለበት።”—ማርቆስ 13:10
እዚህ ላይ የተጠቀሰው ‘ምሥራች’ ይሖዋ መከራን እንደሚያስወግድ፣ ምድርን ገነት እንደሚያደርግና በሞት የተለዩንን ሰዎች እንደሚያስነሳ የሰጠውን ተስፋ ያካትታል። የይሖዋ ምሥክሮች ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት በዓለም ዙሪያ እየሰበኩ ነው።