የጥናት ፕሮጀክት
መንፈሳዊ ሰዎች ጥሩ ውሳኔ ያደርጋሉ
ዘፍጥረት 25:29-34ን አንብብ፤ ከዚያም ከኤሳውና ከያዕቆብ ጥሩ ውሳኔ ያደረገው ማን እንደሆነ ተመልከት።
ስለ አውዱ በጥልቀት ምርምር አድርግ። ከዚያ በፊት ምን ተከናውኗል? (ዘፍ. 25:20-28) ከዚያ በኋላስ?—ዘፍ. 27:1-46
በዝርዝር ጉዳዮቹ ላይ በጥልቀት ምርምር አድርግ። በዚያ ዘመን የበኩር ልጆች የትኞቹ መብቶችና ኃላፊነቶች ነበሯቸው?—ዘፍ. 18:18, 19፤ w10 5/1 13
-
አንድ ሰው የመሲሑ ቅድመ አያት ለመሆን የግድ የበኩር ልጅ መሆን ይጠበቅበት ነበር? (w17.12 14-15)
ትምህርቱን ለማስተዋል ሞክር፤ ከዚያም በሥራ ላይ አውል። ያዕቆብ ለብኩርና መብት ከኤሳው የበለጠ ቦታ የሰጠው ለምንድን ነው? (ዕብ. 12:16, 17፤ w03 10/15 28-29) ይሖዋ ለሁለቱ ወንድማማቾች ምን አመለካከት ነበረው? ለምንስ? (ሚል. 1:2, 3) ኤሳው የተሻለ ውሳኔ ማድረግ የሚችለው ምን ቢያደርግ ነበር?
-
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ በሳምንታዊ ፕሮግራሜ ላይ፣ ለምሳሌ ለቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራም ሳወጣ ለመንፈሳዊ ነገሮች አድናቆት እንዳለኝ ማሳየት የምችለው እንዴት ነው?