የሚወደን ፈጣሪያችን ያስብልናል
1. ፈጣሪያችን ፀሐይን ያወጣል
2. ፈጣሪያችን ዝናብ ያዘንባል
3. ፈጣሪያችን ምግብና ልብስ ይሰጠናል
ብዙ አባቶች ለቤተሰባቸው በቂ ምግብና ልብስ የማቅረብ ጉዳይ ያስጨንቃቸዋል። ቅዱሳን መጻሕፍት ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚሉ እንመልከት፦ “የሰማይ ወፎችን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ እነሱ አይዘሩም፣ አያጭዱም ወይም በጎተራ አያከማቹም፤ ይሁንና በሰማይ ያለው አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከእነሱ አትበልጡም?”—ማቴዎስ 6:25, 26
“እስቲ የሜዳ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ . . . ያን ያህል ክብር የነበረው [ንጉሥ] ሰለሞን እንኳ ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዷ አላጌጠም። አምላክ . . . የሜዳ [ተክልን] እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ . . . እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም?”—ማቴዎስ 6:28-30
አምላክ ምግብና ልብስ ሊሰጠን የሚችል ከሆነ ለሕይወት የሚያስፈልጉንን ሌሎች ነገሮችም ለማግኘት እንደሚረዳን ልንጠራጠር አይገባም። የእሱን ፈቃድ እስካደረግን ድረስ አምላክ፣ አርሰን ምግባችንን ለማምረት የምናደርገውን ጥረት ይባርክልናል፤ አሊያም የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለመግዛት የሚያስችለንን ሥራ እንድናገኝ ይረዳናል።—ማቴዎስ 6:32, 33
በእርግጥም ስለ ፀሐይ፣ ስለ ዝናብ፣ ስለ ወፎችና ስለ አበቦች ስናስብ አምላክን ለመውደድ እንነሳሳለን። በቀጣዩ ርዕስ ላይ ፈጣሪ ለሰው ልጆች መልእክት ያስተላለፈው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።