ሁለተኛ ዜና መዋዕል 27:1-9

  • ኢዮዓታም በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-9)

27  ኢዮዓታም+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ16 ዓመት ገዛ። እናቱም የሩሻህ ትባል ነበር፤ እሷም የሳዶቅ ልጅ ነበረች።+ 2  ኢዮዓታም አባቱ ዖዝያ እንዳደረገው ሁሉ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ፤+ ይሁንና ሥርዓቱን ጥሶ ወደ ይሖዋ ቤተ መቅደስ አልገባም።+ ሕዝቡ ግን ክፉ ድርጊት መፈጸሙን አልተወም ነበር። 3  እሱም የይሖዋን ቤት+ የላይኛውን በር ሠራ፤ በኦፌልም+ ቅጥር ላይ መጠነ ሰፊ የግንባታ ሥራ አከናወነ። 4  በተጨማሪም በተራራማው የይሁዳ ክልል+ ከተሞችን ሠራ፤+ በደን በተሸፈኑት ስፍራዎችም ምሽጎችንና+ ማማዎችን+ ገነባ። 5  ከአሞናውያንም ንጉሥ ጋር ተዋጋ፤+ በመጨረሻም አሸነፋቸው፤ በመሆኑም አሞናውያን በዚያ ዓመት 100 የብር ታላንት፣* 10,000 የቆሮስ መስፈሪያ* ስንዴና 10,000 የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ ሰጡት። በተጨማሪም አሞናውያን በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ይህንኑ ግብር አመጡለት።+ 6  ኢዮዓታም በአምላኩ በይሖዋ ፊት መንገዱን ስላጸና* ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ ሄደ። 7  የቀረው የኢዮዓታም ታሪክ፣ ያካሄዳቸው ጦርነቶችና የተከተለው መንገድ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈዋል።+ 8  እሱ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 25 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ16 ዓመት ገዛ።+ 9  በመጨረሻም ኢዮዓታም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም+ ቀበሩት። በእሱም ምትክ ልጁ አካዝ ነገሠ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

አንድ ታላንት 34.2 ኪሎ ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
አንድ ቆሮስ 220 ሊትር ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ስላዘጋጀ።”