በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የዘዳግም መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • ከኮሬብ ተራራማ አካባቢ ተነስተው ተጓዙ (1-8)

    • አለቆችና ዳኞች ተሾሙ (9-18)

    • በቃዴስበርኔ የተፈጸመው ዓመፅ (19-46)

      • እስራኤላውያን ወደ ምድሪቱ ለመግባት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ (26-33)

      • ከነአንን ድል ለመምታት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ቀረ (41-46)

  • 2

    • ለ38 ዓመት በምድረ በዳ ተንከራተቱ (1-23)

    • የሃሽቦንን ንጉሥ ሲሖንን ድል አደረጉ (24-37)

  • 3

    • የባሳንን ንጉሥ ኦግን ድል አደረጉ (1-7)

    • ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን ምድር ተከፋፈሉ (8-20)

    • ኢያሱ እንዳይፈራ ማበረታቻ ተሰጠው (21, 22)

    • ሙሴ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደማይገባ ተነገረው (23-29)

  • 4

    • ታዛዦች እንዲሆኑ የቀረበ ጥሪ (1-14)

      • አምላክ ያደረገላችሁን ነገር አትርሱ (9)

    • ይሖዋ እሱ ብቻ እንዲመለክ ይፈልጋል (15-31)

    • እንደ ይሖዋ ያለ አምላክ የለም (32-40)

    • ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያሉ የመማጸኛ ከተሞች (41-43)

    • ሙሴ ለእስራኤላውያን ሕጉን ነገራቸው (44-49)

  • 5

    • ይሖዋ በኮሬብ ከእስራኤላውያን ጋር የገባው ቃል ኪዳን (1-5)

    • አሥርቱ ትእዛዛት በድጋሚ ተዘረዘሩ (6-22)

    • በሲና ተራራ አጠገብ ሕዝቡ ፍርሃት አደረበት (23-33)

  • 6

    • ይሖዋን በሙሉ ልብ ውደድ (1-9)

      • “እስራኤል ሆይ ስማ” (4)

      • ወላጆች ልጆቻቸውን ማስተማር ይጠበቅባቸዋል (6, 7)

    • አምላክህን ይሖዋን አትርሳ (10-15)

    • ይሖዋን አትፈታተን (16-19)

    • ለቀጣዩ ትውልድ ተናገር (20-25)

  • 7

    • መጥፋት ያለባቸው ሰባት ብሔራት (1-6)

    • እስራኤላውያን የተመረጡበት ምክንያት (7-11)

    • ታዛዥነት በረከት ያስገኛል (12-26)

  • 8

    • የይሖዋ በረከት (1-9)

      • ‘ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም’ (3)

    • አምላክህን ይሖዋን አትርሳ (10-20)

  • 9

    • እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር የገቡት በጽድቃቸው አይደለም (1-6)

    • እስራኤላውያን ይሖዋን አራት ጊዜ አስቆጡት (7-29)

      • የወርቅ ጥጃ (7-14)

      • ሙሴ ያቀረበው ምልጃ (15-21, 25-29)

      • ይሖዋን ሦስት ጊዜ አስቆጡት (22)

  • 10

    • ሙሴ በድጋሚ ሁለት ጽላቶችን አዘጋጀ (1-11)

    • ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? (12-22)

      • ይሖዋን መፍራትና መውደድ (12)

  • 11

    • የይሖዋን ታላቅነት አይተሃል (1-7)

    • ተስፋይቱ ምድር (8-12)

    • ታዛዥነት የሚያስገኘው በረከት (13-17)

    • የአምላክ ቃል በልብህ ላይ ይታተም (18-25)

    • “በረከትና እርግማን” (26-32)

  • 12

    • አምላክ በሚመርጠው ስፍራ የሚቀርብ አምልኮ (1-14)

    • ሥጋ እንዲበሉ ቢፈቀድላቸውም ደም እንዳይበሉ ታዘዋል (15-28)

    • በሌሎች አማልክት እንዳትጠመድ ተጠንቀቅ (29-32)

  • 13

    • ከሃዲዎችን በተመለከተ መደረግ ያለበት ነገር (1-18)

  • 14

    • ሐዘንን ለመግለጽ ተብለው የሚደረጉ ተገቢ ያልሆኑ ነገሮች (1, 2)

    • ንጹሕ የሆነና ንጹሕ ያልሆነ ምግብ (3-21)

    • አንድ አሥረኛውን ለይሖዋ መስጠት (22-29)

  • 15

    • በየሰባት ዓመቱ ዕዳ ይሰረዛል (1-6)

    • ድሆችን መርዳት (7-11)

    • በየሰባት ዓመቱ ባሮች ነፃ ይወጣሉ (12-18)

      • የባሪያን ጆሮ በወስፌ መብሳት (16, 17)

    • የእንስሳትን በኩር መቀደስ (19-23)

  • 16

    • ፋሲካ፤ እርሾ ያልገባበት ቂጣ በዓል (1-8)

    • የሳምንታት በዓል (9-12)

    • የዳስ በዓል (13-17)

    • ዳኞች ተሾሙ (18-20)

    • የማምለኪያ ግንድና ዓምድ አታቁም (21, 22)

  • 17

    • የሚቀርበው መሥዋዕት እንከን የለሽ መሆን አለበት (1)

    • ከሃዲዎችን በተመለከተ መደረግ ያለበት ነገር (2-7)

    • ለመዳኘት አስቸጋሪ የሆኑ የፍርድ ጉዳዮች (8-13)

    • ወደፊት ንጉሥ ቢያነግሡ መደረግ ያለበት ነገር (14-20)

      • ንጉሡ የሕጉን ቅጂ ለራሱ መገልበጥ ይኖርበታል (18)

  • 18

    • የካህናቱና የሌዋውያኑ ድርሻ (1-8)

    • መናፍስታዊ ድርጊቶች የተከለከሉ ናቸው (9-14)

    • እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ (15-19)

    • ሐሰተኛ ነቢያትን ለይቶ ማወቅ (20-22)

  • 19

    • የደም ዕዳና የመማጸኛ ከተሞች (1-13)

    • ወሰን አትግፋ (14)

    • ዳኛ ፊት ቀርቦ መመሥከር (15-21)

      • ሁለት ወይም ሦስት ምሥክሮች ያስፈልጋሉ (15)

  • 20

    • ለጦርነት በሚወጡበት ጊዜ ሊከተሉት የሚገባው ሕግ (1-20)

      • ከወታደራዊ አገልግሎት ነፃ መሆን (5-9)

  • 21

    • ገዳዩ ስላልታወቀ ሰው የተሰጠ መመሪያ (1-9)

    • የተማረከችን ሴት ስለማግባት (10-14)

    • የበኩር ልጅ መብት (15-17)

    • እልኸኛና ዓመፀኛ ልጅ (18-21)

    • በእንጨት ላይ የሚሰቀል ሰው የተረገመ ነው (22, 23)

  • 22

    • ለባልንጀራህ እንስሳ አሳቢነት አሳይ (1-4)

    • ሴት የወንድ ልብስ፣ ወንድ ደግሞ የሴት ልብስ አይልበሱ (5)

    • ለእንስሳት አሳቢነት ማሳየት (6, 7)

    • በጣሪያህ ዙሪያ መከታ ሥራ (8)

    • አትቀላቅል (9-11)

    • በልብስህ ላይ ዘርፍ አድርግ (12)

    • የፆታ ጥቃትን አስመልክቶ የተሰጠ ሕግ (13-30)

  • 23

    • ወደ አምላክ ጉባኤ መግባት የሌለባቸው (1-8)

    • የሰፈሩን ንጽሕና መጠበቅ (9-14)

    • ከጌታው የኮበለለ ባሪያ (15, 16)

    • ዝሙት አዳሪነት የተከለከለ ነው (17, 18)

    • ወለድና ስእለት (19-23)

    • እሸት ቀጥፎ ስለመብላት (24, 25)

  • 24

    • ጋብቻና ፍቺ (1-5)

    • ለሕይወት አክብሮት ማሳየት (6-9)

    • ለድሆች አሳቢነት ማሳየት (10-18)

    • የቃርሚያ ሕግ (19-22)

  • 25

    • የግርፋት ሕግ (1-3)

    • የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር (4)

    • የወንድምን ሚስት ማግባት (5-10)

    • በጠብ ጊዜ ተገቢ ያልሆነን የሰውነት ክፍል መያዝ (11, 12)

    • ትክክለኛ ሚዛንና መለኪያ (13-16)

    • አማሌቃውያን መጥፋት አለባቸው (17-19)

  • 26

    • የፍሬ በኩራትን መባ አድርጎ ማቅረብ (1-11)

    • ለሁለተኛ ጊዜ የሚሰጥ አሥራት (12-15)

    • እስራኤል የይሖዋ ልዩ ንብረት ነው (16-19)

  • 27

    • ሕጉ በድንጋዮች ላይ መጻፍ ይኖርበታል (1-10)

    • በኤባልና በገሪዛን ተራራ ላይ (11-14)

    • እርግማኑ ተነበበ (15-26)

  • 28

    • መታዘዝ የሚያስገኘው በረከት (1-14)

    • አለመታዘዝ የሚያስከትለው እርግማን (15-68)

  • 29

    • በሞዓብ ምድር የተገባው ቃል ኪዳን (1-13)

    • አለመታዘዝን አስመልክቶ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ (14-29)

      • የተሰወሩና የተገለጡ ነገሮች (29)

  • 30

    • ወደ ይሖዋ መመለስ (1-10)

    • የይሖዋ ትእዛዛት ከባድ አይደሉም (11-14)

    • ከሕይወትና ከሞት አንዱን መምረጥ (15-20)

  • 31

    • ሙሴ ሊሞት ሲቃረብ (1-8)

    • ሕጉን በሕዝብ ፊት ስለ ማንበብ የተሰጠ መመሪያ (9-13)

    • ኢያሱ በሙሴ እግር ተተካ (14, 15)

    • እስራኤላውያን እንደሚያምፁ ትንቢት ተነገረ (16-30)

      • እስራኤላውያን ሊማሩት የሚገባቸው መዝሙር (19, 22, 30)

  • 32

    • የሙሴ መዝሙር (1-47)

      • ይሖዋ ዓለት ነው (4)

      • እስራኤል ዓለት የሆነለትን አምላክ ረሳ (18)

      • ‘በቀል የእኔ ነው’ (35)

      • “እናንተ ብሔራት ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ” (43)

    • ሙሴ በነቦ ተራራ ላይ እንደሚሞት ተነገረው (48-52)

  • 33

    • ሙሴ የእስራኤልን ነገዶች ባረከ (1-29)

      • የይሖዋ ‘ዘላለማዊ ክንዶች’ (27)

  • 34

    • ይሖዋ ለሙሴ ምድሪቱን አሳየው (1-4)

    • ሙሴ ሞተ (5-12)