ዘኁልቁ 25:1-18
25 እስራኤላውያን በሺቲም+ ይኖሩ በነበረበት ጊዜ ሕዝቡ ከሞዓብ ሴቶች ጋር የፆታ ብልግና መፈጸም ጀመረ።+
2 ሴቶቹም ለአማልክታቸው ወደተሠዉት መሥዋዕቶች ሕዝቡን ጠሩ፤+ ሕዝቡም ከመሥዋዕቱ መብላት እንዲሁም ለእነሱ አማልክት መስገድ ጀመረ።+
3 ስለዚህ እስራኤል የፌጎርን ባአል በማምለክ ተባበረ፤*+ ይሖዋም በእስራኤል ላይ እጅግ ተቆጣ።
4 ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እየነደደ ያለው የይሖዋ ቁጣ ከእስራኤል ላይ እንዲመለስ የዚህን ሕዝብ መሪዎች* ሁሉ ወስደህ በጠራራ ፀሐይ* በይሖዋ ፊት ስቀላቸው።”
5 ከዚያም ሙሴ የእስራኤልን ዳኞች+ “እያንዳንዳችሁ በፌጎር ባአል አምልኮ የተባበረውን* የየራሳችሁን ሰው ግደሉ” አላቸው።+
6 ሆኖም ልክ በዚህ ጊዜ አንድ እስራኤላዊ፣ ሙሴና በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ እያለቀሰ ያለው የእስራኤል ማኅበረሰብ በሙሉ እያዩት አንዲት ምድያማዊት ሴት+ ይዞ ወደ ወንድሞቹ መጣ።
7 የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ+ ይህን ሲመለከት ከማኅበረሰቡ መሃል ወዲያው ብድግ ብሎ ጦር አነሳ።
8 ከዚያም እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ ድንኳኑ በመግባት ሁለቱንም ወጋቸው፤ እስራኤላዊውን ወጋው፤ እሷንም ሆዷ* ላይ ወጋት። በዚህ ጊዜ መቅሰፍቱ ከእስራኤል ልጆች ላይ ተወገደ።+
9 በመቅሰፍቱ የሞቱት ሰዎች 24,000 ነበሩ።+
10 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦
11 “የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ+ በመካከላቸው እኔን የሚቀናቀነኝን ማንኛውንም ነገር በቸልታ ባለማለፉ ቁጣዬ ከእስራኤል ሕዝብ ላይ እንዲመለስ አድርጓል።+ ስለዚህ እስራኤላውያንን እኔን ብቻ ለምን አላመለካችሁም ብዬ ጠራርጌ አላጠፋኋቸውም።+
12 በዚህም የተነሳ ከእሱ ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እንደምገባ ንገረው።
13 ይህም አምላኩን የሚቀናቀነውን ማንኛውንም ነገር በቸልታ ባለማለፉ+ እንዲሁም ለእስራኤል ሕዝብ በማስተሰረዩ ለእሱና ከእሱ በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ+ ዘላቂ የክህነት ቃል ኪዳን ሆኖ ያገለግላል።”
14 ከምድያማዊቷ ሴት ጋር የተገደለው ሟቹ እስራኤላዊ የስምዖናውያን አባቶች ቤት አለቃ የሆነው የሳሉ ልጅ ዚምሪ ነበር።
15 የተገደለችውም ምድያማዊት ሴት የጹር+ ልጅ ኮዝቢ ነበረች፤ ጹር በምድያም ካሉት የአባቶች ቤት ጎሳዎች የአንዱ መሪ ነበር።+
16 በኋላም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦
17 “ምድያማውያንን አንገላቷቸው፤ እንዲሁም ፍጇቸው፤+
18 ምክንያቱም እነሱ ከፌጎርና+ ከእህታቸው ከኮዝቢ ጋር በተያያዘ በፈጸሙባችሁ ተንኮል የተነሳ አንገላተዋችኋል፤ ኮዝቢ ከፌጎር ጋር በተያያዘ የተከሰተው መቅሰፍት በመጣበት ዕለት+ የተገደለች የምድያማዊው አለቃ ልጅ ነች።”+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ከፌጎር ባአል ጋር ተጣበቀ።”
^ ቃል በቃል “ራሶች።”
^ ቃል በቃል “በፀሐይ ፊት።”
^ ወይም “ከፌጎር ባአል ጋር የተጣበቀውን።”
^ “ብልቷ” ላቲን ቩልጌት። “ማህፀኗ” የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም።