ሚልክያስ 4:1-6

  • ከይሖዋ ቀን በፊት ኤልያስ ይመጣል (1-6)

    • ‘የጽድቅ ፀሐይ ትወጣለች’ (2)

4  “እነሆ፣ ያ ቀን እንደ ምድጃ እየነደደ ይመጣል፤+ በዚያ ጊዜ እብሪተኞች ሁሉና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ እንደ ገለባ ይሆናሉ። የሚመጣው ቀን በእርግጥ ይበላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ሥርም ሆነ ቅርንጫፍ አይተውላቸውም። 2  ስሜን ለምታከብሩት* ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሐይ በጨረሮቿ* ፈውስ ይዛ ትወጣለች፤ እናንተም እንደሰቡ ጥጆች ትቦርቃላችሁ።” 3  “እኔም እርምጃ በምወስድበት ቀን ክፉዎችን ትረግጣላችሁ፤ ከእግራችሁ ሥር እንዳለ አቧራ ይሆናሉና” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 4  “የአገልጋዬን የሙሴን ሕግ ይኸውም መላው እስራኤል እንዲያከብረው በኮሬብ ያዘዝኩትን ሥርዓትና ድንጋጌ አስታውሱ።+ 5  “እነሆ፣ ታላቁና የሚያስፈራው የይሖዋ ቀን ከመምጣቱ በፊት+ ነቢዩ ኤልያስን እልክላችኋለሁ።+ 6  እሱም መጥቼ ምድርን እንዳልመታና ፈጽሜ እንዳላጠፋ የአባቶችን ልብ እንደ ልጆች ልብ፣+ የልጆችንም ልብ እንደ አባቶች ልብ ያደርጋል።”*

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “ለምትፈሩት።”
ቃል በቃል “በክንፎቿ።”
ወይም “የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፣ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።”