መዝሙር 95:1-11

  • ታዛዥነት የታከለበት እውነተኛ አምልኮ

    • “ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ” (7)

    • “ልባችሁን አታደንድኑ” (8)

    • “ወደ እረፍቴ አይገቡም” (11)

95  ኑ፣ ለይሖዋ እልል እንበል! አዳኛችን ለሆነው ዓለት በድል አድራጊነት ስሜት እልል እንበል።+  2  ምስጋና ይዘን በፊቱ እንቅረብ፤+በድል አድራጊነት ስሜት ለእሱ እንዘምር፤ ደግሞም እልል እንበል።  3  ይሖዋ ታላቅ አምላክ ነውና፤በሌሎች አማልክት ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።+  4  ጥልቅ የሆኑት የምድር ክፍሎች በእጁ ናቸው፤የተራሮችም ጫፍ የእሱ ነው።+  5  እሱ የሠራው ባሕር የራሱ ነው፤+የብሱንም የሠሩት እጆቹ ናቸው።+  6  ኑ፣ እናምልክ፤ እንስገድም፤ሠሪያችን በሆነው በይሖዋ ፊት እንንበርከክ።+  7  እሱ አምላካችን ነውና፤እኛ ደግሞ በመስኩ የተሰማራን ሕዝቦች፣በእሱ እንክብካቤ* ሥር ያለን በጎች ነን።+ ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ፣+  8  አባቶቻችሁ በምድረ በዳ ሳሉ በመሪባ፣*በማሳህ* ቀን እንዳደረጉት ልባችሁን አታደንድኑ፤+  9  በዚያን ጊዜ እነሱ ፈተኑኝ፤+ሥራዬን ቢያዩም ተገዳደሩኝ።+ 10  ያን ትውልድ ለ40 ዓመት ተጸየፍኩት፤እኔም “ይህ ሕዝብ ሁልጊዜ ልቡ ይስታል፤መንገዴን ሊያውቅ አልቻለም” አልኩ። 11  በመሆኑም “ወደ እረፍቴ አይገቡም” ብዬ በቁጣዬ ማልኩ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “በእጁ።”
“ጠብ” የሚል ትርጉም አለው።
“ፈተና፤ ፈታኝ ሁኔታ” የሚል ትርጉም አለው።