መዝሙር 81:1-16
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በጊቲት።* የአሳፍ+ መዝሙር።
81 ብርታታችን ለሆነው አምላክ+ እልል በሉ።
ለያዕቆብ አምላክ በድል አድራጊነት ስሜት ጩኹ።
2 ሙዚቃውን መጫወት ጀምሩ፤ አታሞም ምቱ፤ደስ የሚያሰኘውን በገና ከባለ አውታር መሣሪያ ጋር ተጫወቱ።
3 አዲስ ጨረቃ በምትታይበት፣ሙሉ ጨረቃም ወጥታ በዓል በምናከብርበት ዕለት+ ቀንደ መለከት ንፉ።+
4 ይህ ለእስራኤል የተሰጠ ድንጋጌ፣የያዕቆብም አምላክ ያስተላለፈው ውሳኔ ነውና።+
5 በግብፅ ምድር ላይ ባለፈ ጊዜ፣+ይህን ለዮሴፍ ማሳሰቢያ አድርጎ ሰጠው።+
እኔም የማላውቀውን ድምፅ* ሰማሁ፦
6 “ሸክሙን ከትከሻው ላይ አነሳሁለት፤+እጆቹ ቅርጫት ከመያዝ አረፉ።
7 በጨነቀህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ታደግኩህ፤+ከነጎድጓዳማው ደመና* መለስኩልህ።+
የመሪባ* ውኃዎች ባሉበት ስፍራ ፈተንኩህ።+ (ሴላ)
8 ሕዝቤ ሆይ፣ ስማኝ፤ እኔም እመሠክርብሃለሁ።
እስራኤል ሆይ፣ ምነው ብታዳምጠኝ!+
9 በመካከልህ እንግዳ አምላክ አይኖርም፤ለባዕድ አምላክም አትሰግድም።+
10 ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።+
አፍህን በሰፊው ክፈት፤ እኔም በምግብ እሞላዋለሁ።+
11 ሕዝቤ ግን ድምፄን አልሰማም፤እስራኤል ለእኔ አይገዛም።+
12 በመሆኑም እልኸኛ ልባቸውን እንዲከተሉ ተውኳቸው፤ትክክል መስሎ የታያቸውን አደረጉ።*+
13 ምነው ሕዝቤ ቢያዳምጠኝ ኖሮ!+ምነው እስራኤል በመንገዴ ቢመላለስ ኖሮ!+
14 ጠላቶቻቸውን ወዲያውኑ ባንበረከክኋቸው፣እጄን በባላጋራዎቻቸው ላይ በሰነዘርኩ ነበር።+
15 ይሖዋን የሚጠሉ በፊቱ ይሸማቀቃሉ፤የሚደርስባቸውም ነገር* ዘላለማዊ ነው።
16 እሱ ግን ምርጡን ስንዴ* ይመግባችኋል፤*+ከዓለት በሚገኝ ማርም ያጠግባችኋል።”+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ ወይም “ቋንቋ።”
^ “ጠብ” የሚል ትርጉም አለው።
^ ቃል በቃል “በነጎድጓድ መሰወሪያ ቦታ።”
^ ቃል በቃል “በምክራቸው ተመላለሱ።”
^ ቃል በቃል “ዘመናቸውም።”
^ ቃል በቃል “የስንዴ ስብ።”
^ ቃል በቃል “ይመግበዋል።” የአምላክን ሕዝብ ያመለክታል።