መዝሙር 71:1-24
71 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ።
ፈጽሞ ለኀፍረት አልዳረግ።+
2 በጽድቅህ አድነኝ፤ ታደገኝም።
ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤* አድነኝም።+
3 ምንጊዜም የምገባበትመሸሸጊያ ዓለት ሁንልኝ።
አንተ ቋጥኜና ምሽጌ ስለሆንክእኔን ለማዳን ትእዛዝ ስጥ።+
4 አምላኬ ሆይ፣ ከክፉው እጅ፣ግፈኛ ከሆነው ጨቋኝ ሰው መዳፍ ታደገኝ።+
5 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ተስፋዬ ነህ፤ከልጅነቴ ጀምሮ በአንተ ታምኛለሁ።*+
6 ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ በአንተ ታምኛለሁ፤ከእናቴ ማህፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ።+
ሁልጊዜ አወድስሃለሁ።
7 ለብዙዎች መደነቂያ ሆንኩ፤አንተ ግን ጽኑ መጠጊያዬ ነህ።
8 አፌ በውዳሴህ ተሞልቷል፤+ቀኑን ሙሉ ስለ ግርማህ እናገራለሁ።
9 በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤+ጉልበቴ በሚያልቅበት ጊዜም አትተወኝ።+
10 ጠላቶቼ በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይናገራሉ፤ሕይወቴን* የሚሹ ሰዎችም በእኔ ላይ ሴራ ይጠነስሳሉ፤+
11 እንዲህም ይላሉ፦ “አምላክ ትቶታል።
የሚያድነው ስለሌለ አሳዳችሁ ያዙት።”+
12 አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።
አምላኬ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+
13 የሚቃወሙኝ* ሰዎችይፈሩ፤ ይጥፉም።+
የእኔን ጥፋት የሚሹውርደትና ኀፍረት ይከናነቡ።+
14 እኔ ግን አንተን መጠባበቄን እቀጥላለሁ፤በውዳሴ ላይ ውዳሴ አቀርብልሃለሁ።
15 አፌ ስለ ጽድቅህ ያወራል፤+ከብዛታቸው የተነሳ ላውቃቸው* ባልችልም እንኳአንደበቴ ስለ ማዳን ሥራዎችህ ቀኑን ሙሉ ይናገራል።+
16 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣መጥቼ ስለ ብርቱ ሥራዎችህ እናገራለሁ፤ስለ አንተ ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ።
17 አምላክ ሆይ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ አስተምረኸኛል፤+እኔም እስካሁን ድረስ ድንቅ ሥራዎችህን አስታውቃለሁ።+
18 አምላክ ሆይ፣ ሳረጅና ስሸብትም እንኳ አትጣለኝ።+
ለቀጣዩ ትውልድ ስለ ብርታትህ፣*ገና ለሚመጡትም ሁሉ ስለ ኃያልነትህ ልናገር።+
19 አምላክ ሆይ፣ ጽድቅህ እጅግ ታላቅ ነው፤+ታላላቅ ነገሮችን አከናውነሃል፤አምላክ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+
20 ብዙ ጭንቅና መከራ ብታሳየኝም እንኳ+እንደገና እንዳንሰራራ አድርገኝ፤ጥልቅ ከሆነው ምድር* አውጣኝ።+
21 ታላቅነቴ ገናና እንዲሆን አድርግ፤ዙሪያዬንም ከበህ አጽናናኝ።
22 እኔም አምላኬ ሆይ፣ ከታማኝነትህ+ የተነሳበባለ አውታር መሣሪያ አወድስሃለሁ።
የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፣በበገና የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።
23 ለአንተ የውዳሴ መዝሙር በምዘምርበት ጊዜ ከንፈሮቼ እልል ይላሉ፤+ሕይወቴን አድነሃታልና።*+
24 ምላሴ ቀኑን ሙሉ ስለ ጽድቅህ ይናገራል፤*+የእኔን መጥፋት የሚሹ ሰዎች ያፍራሉና፤ ደግሞም ይዋረዳሉ።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ጎንበስ ብለህ ስማኝ።”
^ ወይም “አንተ መመኪያዬ ነህ።”
^ ወይም “ነፍሴን።”
^ ወይም “ነፍሴን የሚቃወሟት።”
^ ወይም “ልቆጥራቸው።”
^ ቃል በቃል “ስለ ክንድህ።”
^ ወይም “በምድር ካሉ ጥልቅ ውኃዎች።”
^ ወይም “ነፍሴን ዋጅተሃታልና።”
^ ወይም “ያሰላስላል።”