መዝሙር 14:1-7
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር።
14 ሞኝ* ሰው በልቡ
“ይሖዋ የለም” ይላል።+
ሥራቸው ብልሹ ነው፤ ተግባራቸውም አስጸያፊ ነው፤መልካም የሚሠራ ማንም የለም።+
2 ሆኖም ጥልቅ ማስተዋል ያለውና ይሖዋን የሚፈልግ ሰው ይኖር እንደሆነ ለማየት፣ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ወደ ሰው ልጆች ይመለከታል።+
3 ሁሉም መንገድ ስተዋል፤+ሁሉም ብልሹ ናቸው።
መልካም የሚሠራ ማንም የለም፤አንድ እንኳ የለም።
4 ከክፉ አድራጊዎቹ መካከል አንዳቸውም አያስተውሉም?
ምግብ እንደሚበሉ ሕዝቤን ይውጣሉ።
ይሖዋን አይጠሩም።
5 ይሁንና በታላቅ ሽብር ይዋጣሉ፤+ይሖዋ ከጻድቅ ትውልድ ጋር ነውና።
6 እናንተ ክፉ አድራጊዎች የችግረኛውን ሰው ዕቅድ ለማጨናገፍ ትሞክራላችሁ፤ይሖዋ ግን መጠጊያው ነው።+
7 የእስራኤል መዳን ምነው ከጽዮን በመጣ!+
ይሖዋ የተማረከውን ሕዝቡን በሚመልስበት ጊዜ፣ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤል ሐሴት ያድርግ።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ማመዛዘን የጎደለው።”