በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ

ለተሰብሳቢዎች የቀረበ መረጃ

መዋጮዎች ስብሰባው አስደሳች ብሎም ይበልጥ ወደ ይሖዋ እንድንቀርብ የሚረዳን እንዲሆን ለማድረግ ሲባል ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ በቂ ወንበሮች እንዲሁም የድምፅ መሣሪያዎችና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶች እንዲኖሩ ዝግጅት ተደርጓል። በፈቃደኝነት የምታደርጉት መዋጮ እነዚህን ወጪዎች ለመሸፈን እንዲሁም ዓለም አቀፉን ሥራ ለመደገፍ አስተዋጽኦ ያበረክታል። “የመዋጮ ሣጥን” የሚል ምልክት በግልጽ የተጻፈባቸው ሣጥኖች በስብሰባው ቦታ አመቺ በሆኑ ስፍራዎች ላይ ተቀምጠዋል። ሆኖም የሚቻል ከሆነ እባካችሁ donate.jw.org ወደተባለው ድረ ገጽ በመሄድ በኢንተርኔት አማካኝነት መዋጮ አድርጉ። የምታደርጉትን መዋጮ ሁሉ ከልብ እናደንቃለን። የበላይ አካሉ የአምላክን መንግሥት ዓላማ ለማራመድ በልግስና ለምታደርጉት ድጋፍ ሁሉ በዚህ አጋጣሚ ምስጋናውን ይገልጻል።

አስተናጋጆች አስተናጋጆች የተመደቡት እናንተን ለመርዳት ነው። ስለዚህ መኪና ማቆምን፣ በመተላለፊያዎች ላይ መቆምን፣ ወንበር መያዝንና ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ የሚሰጧችሁን መመሪያ በመከተል እባካችሁ ሙሉ በሙሉ ተባበሯቸው።

ወንበር እባካችሁ ለሌሎች አሳቢነት አሳዩ። ወንበር መያዝ የሚቻለው ለቤተሰባችሁ አባላት፣ ከእናንተ ጋር በመኪና ለሚመጡ፣ አብረዋችሁ ለሚኖሩ ወይም በአሁኑ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ለምታስጠኗቸው ሰዎች ብቻ መሆኑን አስታውሱ። እባካችሁ ከያዛችሁት ቦታ ውጭ በሌሎች ወንበሮች ላይ ዕቃዎቻችሁን አታስቀምጡ።

የመጀመሪያ ደረጃ የሕምክና እርዳታ ይህ ዝግጅት የተደረገው ድንገት ለሚያጋጥም የጤና ችግር ብቻ እንደሆነ እባካችሁ አስታውሱ።

የፈቃደኛ አገልግሎት ከክልል ስብሰባው ጋር በተያያዘ በሚከናወኑ የተለያዩ ሥራዎች መካፈል ከፈለጋችሁ እባካችሁ ለፈቃደኛ አገልግሎት ክፍል አመልክቱ።

ጠፍተው የተገኙ ዕቃዎች የሚቀመጡበት ቦታ ጠፍተው የተገኙ ዕቃዎች ሁሉ ወደዚህ ክፍል መምጣት አለባቸው። ዕቃ ከጠፋባችሁ ወደዚህ ክፍል በመሄድ ንብረታችሁን ጠይቃችሁ መውሰድ ትችላላችሁ። ከወላጆቻቸው የጠፉ ልጆች ወደዚህ ክፍል መወሰድ አለባቸው። ሆኖም በማንም ላይ አላስፈላጊ ጫና እንዳይፈጠር እባካችሁ ልጆቻችሁን በቅርብ ተከታተሏቸው እንዲሁም ከአጠገባችሁ እንዳይርቁ ጠብቋቸው።

ጥምቀት የተለየ ዝግጅት ካልተደረገ በቀር ተጠማቂዎቹ የሚቀመጡት ከመድረኩ ፊት ለፊት ባለው ቦታ ላይ ይሆናል። የጥምቀት ዕጩዎች ቅዳሜ ጠዋት የሚቀርበው የጥምቀት ንግግር ከመጀመሩ በፊት በተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ መገኘት አለባቸው። እያንዳንዱ ተጠማቂ ለጥምቀት ተስማሚ የሆነ ልብስና ፎጣ ይዞ መምጣት አለበት።

በይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል የተዘጋጀ

© 2024 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania