አረጋውያን፤ እርጅና
ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ ምን ይከሰታል?
በተጨማሪም “ማጽናኛ—በሕመም ወይም በእርጅና ምክንያት አቅማችን ሲገደብ” የሚለውን ተመልከት
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
መክ 12:1-8—ንጉሥ ሰለሞን በእርጅና ምክንያት የሚመጡ አንዳንድ እክሎችን በዘይቤ ገልጿል፤ ለምሳሌ የዓይን መድከም (“በመስኮት የሚያዩ ወይዛዝርትም ይጨልምባቸዋል”) እና የጆሮ መድከም (“ሴቶች ልጆችም ሁሉ ዝግ ባለ ድምፅ ይዘምራሉ”)
-
አረጋውያን በእርጅና ምክንያት የሚመጡ ችግሮች እያሉም እንዲሁም አቅማቸው ቢደክምም ደስታቸውን ጠብቀው መኖር ይችላሉ?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
1ሳሙ 12:2, 23—አረጋዊው ነቢይ ሳሙኤል ለይሖዋ ሕዝቦች መጸለዩን መቀጠሉ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ተገንዝቧል
-
2ሳሙ 19:31-39—ንጉሥ ዳዊት አረጋዊው ቤርዜሊ ላሳየው ታማኝነትና ላደረገለት ድጋፍ አመስጋኝ ነበር፤ ቤርዜሊም ዳዊት ያቀረበለትን ግብዣ ለመቀበል አቅሙ እንደማይፈቅድለት በመግለጽ ልኩን እንደሚያውቅ አሳይቷል
-
መዝ 71:9, 18—ንጉሥ ዳዊት ካረጀ በኋላ በይሖዋ ዘንድ ጠቃሚነቱን እንዳያጣ ሰግቶ ነበር፤ በመሆኑም ‘አትጣለኝ’ ብሎ ይሖዋን ለምኖታል፤ ለቀጣዩ ትውልድ ስለ እሱ ለመናገር ብርታት እንዲሰጠውም ጠይቋል
-
ሉቃስ 2:36-38—መበለት የነበረችው አረጋዊቷ ነቢዪት ሐና፣ ለአምላክ ያደረች በመሆኗ እና እሱን በታማኝነት በማገልገሏ ተባርካለች
-
ይሖዋ አረጋውያንን ከፍ አድርጎ እንደሚመለከታቸው ያረጋገጠላቸው እንዴት ነው?
መዝ 92:12-14፤ ምሳሌ 16:31፤ 20:29፤ ኢሳ 46:4፤ ቲቶ 2:2-5
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዘፍ 12:1-4—ይሖዋ ለአብርሃም ሕይወቱን የሚቀይር ተልእኮ የሰጠው የ75 ዓመት ሰው ሳለ ነው
-
ዳን 10:11, 19፤ 12:13—አንድ መልአክ በ90ዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለውን ዳንኤልን አነጋግሮታል፤ በይሖዋ ዘንድ የተወደደ እንደሆነና ለታማኝነቱ ወሮታ እንደሚያገኝ ገልጾለታል
-
ሉቃስ 1:5-13—ይሖዋ አረጋውያኑን ዘካርያስንና ኤልሳቤጥን በተአምር ዮሐንስን እንዲወልዱ በማድረግ ባርኳቸዋል
-
ሉቃስ 2:25-35—ይሖዋ፣ መሲሕ የሚሆነውን ሕፃን እንዲያይ በማድረግ አረጋዊውን ስምዖንን ባርኮታል፤ ስምዖን በመንፈስ መሪነት ስለ መሲሑ ትንቢት ተናግሯል
-
ሥራ 7:23, 30-36—ነቢዩ ሙሴ የይሖዋ ሕዝብ የሆኑትን እስራኤላውያንን እንዲመራ ኃላፊነት የተሰጠው በ80 ዓመቱ ነው
-
ታማኝ የሆኑ አረጋውያንን እንዴት ልንይዛቸው ይገባል?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዘፍ 45:9-11፤ 47:12—ዮሴፍ አረጋዊው አባቱ ያዕቆብ ወደ እሱ እንዲመጣ አድርጓል፤ እስከ ዕለተ ሞቱም ተንከባክቦታል
-
ሩት 1:14-17፤ 2:2, 17, 18, 23—ሩት አረጋዊቷን ናኦሚን በንግግርም ሆነ በተግባር ደግፋታለች
-
ዮሐ 19:26, 27—ኢየሱስ እንጨት ላይ ተሰቅሎ እያጣጣረ በነበረበት ወቅት እናቱን እንዲንከባከብለት የሚወደውን ሐዋርያ ዮሐንስን አደራ ብሎታል
-
ክርስቲያኖች በጉባኤ ውስጥ ያሉ አረጋውያንን ማገዝ የሚችሉባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?