በዓላት
ክርስቲያኖች የሚያከብሯቸው በዓላት
ክርስቲያኖች እንዲያከብሩት የታዘዙት ብቸኛው በዓል የቱ ነው?
የአምላክ አገልጋዮች ለአምልኮ መሰብሰብ ያስደስታቸዋል
ክርስቲያኖች የማያከብሯቸው በዓላት
ከሐሰት ሃይማኖት ጋር ንክኪ ያላቸውን በዓላት ማክበር የሌለብን ለምንድን ነው?
1ቆሮ 10:21፤ 2ቆሮ 6:14-18፤ ኤፌ 5:10, 11
በተጨማሪም “ሃይማኖትን መቀላቀል” የሚለውን ተመልከት
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዘፀ 32:1-10—እስራኤላውያን የሐሰት ሃይማኖት ልማዶችን ከእውነተኛው ሃይማኖት ጋር ለመቀላቀል መሞከራቸው ይሖዋን አስቆጥቶታል
-
ዘኁ 25:1-9—ይሖዋ፣ ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶች አረማዊ በሆኑ ሃይማኖታዊ በዓላት በመካፈላቸውና የሥነ ምግባር ብልግና በመፈጸማቸው ቀጥቷቸዋል
-
ገና የክርስቲያኖች በዓል ነው?
ክርስቲያኖች ልደት ሊያከብሩ ይገባል?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዘፍ 40:20-22—ጣዖት አምላኪው ፈርዖን ልደቱን አክብሯል፤ በዕለቱም ሰው አስገድሏል
-
ማቴ 14:6-11—የክርስቶስ ተከታዮች ጠላት የሆነው ክፉው ንጉሥ ሄሮድስ ልደቱን ባከበረበት ዕለት መጥምቁ ዮሐንስ እንዲገደል አድርጓል
-
የሙሴ ሕግ የሚያዝዛቸው በዓላት
ክርስቲያኖች የሙሴ ሕግ የሚያዝዛቸውን በዓላት እንዲያከብሩ ይጠበቅባቸዋል?
በተጨማሪም ገላ 4:4, 5, 9-11፤ ዕብ 8:7-13፤ 9:1-3, 9, 10, 24ን ተመልከት
ክርስቲያኖች ሳምንታዊውን ሰንበት እንዲያከብሩ ይጠበቅባቸዋል?
በተጨማሪም ዘፀ 31:16, 17ን ተመልከት
ብሔራዊ በዓላት
ክርስቲያኖች በአንድ አገር ታሪክ ውስጥ ወሳኝ ፖለቲካዊ ክንውኖች በሚታሰቡባቸው በዓላት ላይ መካፈላቸው ተገቢ ነው?
በተጨማሪም “መንግሥታት—ክርስቲያኖች ገለልተኞች ናቸው” የሚለውን ተመልከት
ክርስቲያኖች በአገራት መካከል የተደረጉ ጦርነቶችን በሚዘክሩ በዓላት ላይ መካፈላቸው ተገቢ ነው?
በተጨማሪም “መንግሥታት—ክርስቲያኖች ገለልተኞች ናቸው” እና “ጦርነት” የሚለውን ተመልከት
ክርስቲያኖች ለታዋቂ ሰዎች አምልኮ አከል ክብር በሚሰጡ በዓላት ላይ መካፈላቸው ተገቢ ነው?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ሥራ 12:21-23—ቀዳማዊ ንጉሥ ሄሮድስ አግሪጳ ከሕዝቡ የተሰጠውን አምልኮ አከል ክብር በመቀበሉ አምላክ ቀጥቶታል
-
ሥራ 14:11-15—ሐዋርያቱ በርናባስና ጳውሎስ፣ ተገቢ ያልሆነና ከልክ ያለፈ ክብር ሲሰጣቸው ለመቀበል ፈቃደኞች አልሆኑም
-
ራእይ 22:8, 9—የይሖዋ መልአክ፣ አምልኮ አከል ክብር ሲሰጠው ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም
-