በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ልብ

ልብ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልብ የአንድን ሰው አስተሳሰብ፣ ዝንባሌ፣ ባሕርይና ስሜቱን ጨምሮ ውስጣዊ ማንነቱን ለማመልከት እንደተሠራበት በምን እናውቃለን?

መዝ 49:3፤ ምሳሌ 16:9፤ ሉቃስ 5:22 ሥራ 2:26

በተጨማሪም ዘዳ 15:7፤ መዝ 19:8⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 9:46-48—ኢየሱስ በሐዋርያቱ ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታን የመመኘት ዝንባሌ ስለተመለከተ እርማት ሰጥቷቸዋል

ልባችንን መጠበቃችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

1ዜና 28:9፤ ምሳሌ 4:23፤ ኤር 17:9

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 6:5-7—የሰው ልብ ወደ ክፋት ማዘንበሉ ግፍ እንዲበዛ አድርጓል፤ በዚህም የተነሳ ይሖዋ ዓለም አቀፍ የጥፋት ውኃ አምጥቷል

    • 1ነገ 11:1-10—ንጉሥ ሰለሞን ልቡን ሳይጠብቅ ቀርቷል፤ ያገባቸው የባዕድ አገር ሴቶች ልቡን ከይሖዋ አርቀውታል

    • ማር 7:18-23—ኢየሱስ በአምላክ ዓይን ሰውን የሚያረክሰው ነገር ሁሉ የሚመነጨው ከልብ እንደሆነ ተናግሯል

ልባችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?

መዝ 19:14፤ ምሳሌ 3:3-6፤ ሉቃስ 21:34፤ ፊልጵ 4:8

በተጨማሪም ዕዝራ 7:8-10፤ መዝ 119:11⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኤፌ 6:14-18፤ 1ተሰ 5:8—ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ መንፈሳዊው የጦር ትጥቅ ሲገልጽ ጥሩርን ጠቅሷል፤ ጥሩር የአንድን ወታደር ልብ እንደሚጠብቅለት ሁሉ ጽድቅ፣ እምነትና ፍቅርም ምሳሌያዊ ልባችንን ይጠብቁልናል

ምሳሌያዊው ልባችን ችግር ይኖርበት እንደሆነና እንዳልሆነ እንዴት ማወቅ እንችላለን?

ምሳሌ 21:2-4፤ ዕብ 3:12

በተጨማሪም ምሳሌ 6:12-14⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 25:1, 2, 17-27—ንጉሥ አሜስያስ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን በይሖዋ ዓይን ትክክል የሆነውን ነገር አድርጓል፤ ሆኖም በሙሉ ልቡ አልነበረም፤ ከጊዜ በኋላ ልቡ በመታበዩና ታማኝነቱን በማጉደሉ ችግር ላይ ወድቋል

    • ማቴ 7:17-20—ኢየሱስ መጥፎ ዛፍ መጥፎ ፍሬ እንደሚያፈራ ሁሉ መጥፎ ልብም መጥፎ ምግባር እንደሚያፈራ ተናግሯል

ጥሩ ልብ እንዲኖረን ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው? ይህን ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው?

ምሳሌ 10:8፤ 15:28፤ ሉቃስ 6:45

በተጨማሪም መዝ 119:97, 104ሮም 12:9-16፤ 1ጢሞ 1:5⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ነገ 20:1-6—ንጉሥ ሕዝቅያስ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ይሖዋ ምሕረት እንዲያደርግለት ሲለምን እሱን በሙሉ ልቡ እንዳገለገለው ጠቅሷል

    • ማቴ 21:28-32—ኢየሱስ የአንድ ሰው ትክክለኛ የልብ ሁኔታ የሚታወቀው አደርጋለሁ ብሎ በሚናገረው ነገር ሳይሆን በተግባር በሚያደርገው ነገር እንደሆነ በምሳሌ አስረድቷል

ይሖዋ ልባችንን እንደሚመረምር ማወቃችን የሚያጽናናን ለምንድን ነው?

1ዜና 28:9፤ ኤር 17:10

በተጨማሪም 1ሳሙ 2:3⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 16:1-13—ነቢዩ ሳሙኤል፣ ይሖዋ በሰዎች መልክና ቁመና እንደማይደለል ከዚህ ይልቅ ልብ ውስጥ ያለውን ጠልቆ እንደሚያይ ተረድቷል

    • 2ዜና 6:28-31—ንጉሥ ሰለሞን፣ ቤተ መቅደሱ ለይሖዋ አገልግሎት በተወሰነበት ወቅት ባቀረበው ጸሎት ላይ አምላክ የሰዎችን ልብ ሙሉ በሙሉ እንደሚያውቅ፣ ይህን የሚያደርገውም በምሕረት ተነሳስቶ እንደሆነ ጠቅሷል