መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስን መመርመር ለምን አስፈለገ?
በዓለም ላይ በስፋት ስለሚታወቀው መጽሐፍ ይኸውም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎችን እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
ክፍል 5
አምላክ አብርሃምንና ቤተሰቡን ባረካቸው
አምላክ፣ ይስሐቅን መሥዋዕት እንዲያደርግ ለአብርሃም ያቀረበው ጥያቄ የሰው ዘር ምን እንዲገነዘብ አድርጓል? ያዕቆብ ከመሞቱ በፊት ምን ትንቢት ተናገረ?
ክፍል 6
ኢዮብ ንጹሕ አቋሙን ጠበቀ
የማሰብ ችሎታ ያላቸው ፍጥረታት በሙሉ የአምላክ ሉዓላዊ ገዥነት ትክክል መሆኑን እንደሚቀበሉ ማሳየት እንደሚችሉ የኢዮብ መጽሐፍ የሚገልጸው እንዴት ነው?
ክፍል 8
የእስራኤል ሕዝብ ወደ ከነዓን ገባ
እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ምድር ሲገቡ ይሖዋ በኢያሪኮ የነበረችው ረዓብና ቤተሰቧ እንዲተርፉ ያደረገው ለምንድን ነው?
ክፍል 9
እስራኤላውያን ንጉሥ እንዲነግሥላቸው ጠየቁ
እስራኤላውያን ንጉሥ እንዲነግሥላቸው ሲጠይቁ ይሖዋ ሳኦልን መረጠው። ይሖዋ፣ ንጉሥ ሳኦልን በዳዊት የተካው ለምንድን ነው?
ክፍል 10
ሰለሞን ጠቢብ ንጉሥ ነበር
ሰለሞን ምን ያህል ጥበበኛ እንደነበር ከሚያሳዩት ነገሮች አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? ሰለሞን ይሖዋን ሲተው ምን አጋጠመው?
ክፍል 11
በመንፈስ መሪነት የተጻፉ አጽናኝና ትምህርት አዘል መዝሙሮች
አምላክ ለሚወዱት ሰዎች እርዳታና መጽናናት እንደሚሰጥ የሚገልጹት የትኞቹ መዝሙሮች ናቸው? ንጉሡ በማሕልየ መሓልይ መጽሐፍ ላይ ምን ሐሳብ አስፍሯል?
ክፍል 12
ለሕይወት መመሪያ የሚሆን አምላካዊ ጥበብ
በምሳሌና በመክብብ መጻሕፍት ውስጥ የሚገኘው በመንፈስ መሪነት የተጻፈ ምክር፣ ጠቃሚ መመሪያ የሚሰጠን እንዲሁም በአምላክ እንድንተማመን የሚረዳን እንዴት እንደሆነ አንብብ።
ክፍል 14
አምላክ በነቢያቱ አማካኝነት ተናገረ
የአምላክ ነቢያት ስለ የትኞቹ ነገሮች ተናግረው ነበር? በተናገሯቸው ትንቢቶች ውስጥ የሚገኙትን አራት ዋና ዋና ጭብጦች አንብብ።
ክፍል 16
መሲሑ መጣ
ይሖዋ፣ ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን ለማሳወቅ በመላእክትና በመጥምቁ ዮሐንስ የተጠቀመው እንዴት ነው? ይሖዋ ራሱ፣ ልጁ መሲሕ መሆኑን ያሳወቀው እንዴት ነው?
ክፍል 17
ኢየሱስ ስለ አምላክ መንግሥት አስተማረ
የኢየሱስ ስብከት ጭብጥ ምን ነበር? ኢየሱስ አገዛዙ በፍቅርና በፍትሕ ላይ የተመሠረተ እንደሚሆን ያሳየው እንዴት ነው?
ክፍል 25
እምነትን፣ ምግባርንና ፍቅርን በተመለከተ የተሰጠ ምክር
አንድ ክርስቲያን እምነት እንዳለው ማሳየት የሚችለው እንዴት ነው? አንድ ሰው አምላክን ከልቡ እንደሚወደው ማሳየት የሚችለው እንዴት ነው?
የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት—አጠቃላይ ይዘት
መሲሕ የሚሆነውና ምድርን እንደገና ገነት የሚያደርጋት ኢየሱስ መሆኑን ይሖዋ ቀስ በቀስ የገለጸው እንዴት ነው?
የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች የጊዜ ቅደም ተከተል
ከ4026 ዓ.ዓ. እስከ 100 ዓ.ም. ገደማ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን የጊዜ ቅደም ተከተል ተመልከት።