የአምላክን ቃል አጥብቀህ ያዝ
ምዕራፍ ሦስት
የአምላክን ቃል አጥብቀህ ያዝ
1. (ሀ) የጥንቶቹ እስራኤላውያን የአምላክን ቃል እውነተኝነት የመመልከት አጋጣሚ ያገኙት እንዴት ነው? (ለ) ይህስ የእኛን ትኩረት የሚስበው ለምንድን ነው?
“አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ መልካም ተስፋ ሁሉ አንዲቱን እንኳ እንዳላስቀረባችሁ፣ በፍጹም ልባችሁ በፍጹም ነፍሳችሁ ታውቃላችሁ፤ አንዱም ሳይቀር ሁሉም ተፈጽሞአል።” (ኢያሱ 23:14-16) ይህ ቃል እስራኤላውያን በተስፋይቱ ምድር ከሰፈሩ በኋላ ኢያሱ ለእስራኤል ሽማግሌዎች የተናገረው ነው። አዎን፣ ይሖዋ የተናገረው ቃል መሬት ጠብ አይልም። ይህ ዘገባም ሆነ የተቀረው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሙሉ በጽሑፍ ሰፍሮ እንዲቆይ የተደረገው “ተስፋ እንዲኖረን” ነው።—ሮሜ 15:4
2. (ሀ) መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ነው የምንለው ለምንድን ነው? (ለ) መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ መሆኑን ማወቃችን ምን ኃላፊነት ያስከትልብናል?
2 መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት 40 የሚያክሉ ሰዎች ቢሆኑም የመጽሐፉ ባለቤት ይሖዋ ነው። ይህ ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈረውን እያንዳንዱን ነገር ያስጻፈው እሱ ነው ማለት ነው? አዎን። ይህን ያደረገው ቅዱስ መንፈሱን ወይም ኃይሉን መሣሪያ አድርጎ በመጠቀም ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ . . . ይኸውም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው” በማለት ተናግሯል። መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ መሆኑን የሚያምኑ በየትኛውም ሥፍራ የሚኖሩ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር የሚከተሉ ከመሆኑም በላይ የሕይወታቸው መመሪያ አድርገው ይጠቀሙበታል።—2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17፤ 1 ተሰሎንቄ 2:13
ሌሎች ለመጽሐፍ ቅዱስ ከፍ ያለ ግምት እንዲኖራቸው እርዳቸው
3. መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል መሆኑን የማያምኑ ሰዎችን ለመርዳት የሚያስችለው ከሁሉ የተሻለው መንገድ ምንድን ነው?
3 ከምናነጋግራቸው ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል መሆኑን ላያምኑ ይችላሉ። እንዲህ ያሉትን ሰዎች ልንረዳቸው የምንችለው እንዴት ነው? ብዙውን ጊዜ ከሁሉ የተሻለው መንገድ መጽሐፍ ቅዱስን ገልጦ በውስጡ የያዘውን ሐሳብ እንዲመለከቱ ማድረግ ነው። “የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነውና፤ በሁለት በኩል ስለት ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ ስለታም ነው፤ . . . የልብንም ሐሳብና ምኞት ይመረምራል።” (ዕብራውያን 4:12) “የእግዚአብሔር ቃል” ላለንበት ዘመን ምንም ትርጉም የሌለው ያለፈ ታሪክ ሳይሆን ሕያው ቃል ነው! የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋዎች ምንም ነገር ሳያግዳቸው ወደ ፍጻሜያቸው ይገሰግሳሉ። እኛ ከምንናገረው ቃል ይልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት የሰዎችን ልብ በመለወጥ ረገድ የላቀ ኃይል አለው።
4. አንዳንድ ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ ያላቸውን አመለካከት እንዲለውጡ የረዳቸው ስለየትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ያገኙት ማብራሪያ ነው? ለምንስ?
4 ብዙዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የአምላክን ስም ማየታቸው መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ እንዲመረምሩ አነሳስቷቸዋል። ሌሎች ደግሞ ስለ ሕይወት ዓላማ፣ አምላክ ክፋት እንዲኖር ስለፈቀደበት ምክንያት፣ በዘመናችን ያሉት ክስተቶች ስላላቸው ትርጉም ወይም ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ስለሚኖረው የዘላለም ሕይወት ተስፋ ምን እንደሚል ሲረዱ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ወስነዋል። ለክፉ መናፍስት ጥቃት የሚያጋልጡ ሃይማኖታዊ ልማዶች ባሉባቸው አገሮች መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ መንስኤ የሆነውን ነገርም ሆነ ከዚህ ችግር መላቀቅ የሚቻልበትን መንገድ በተመለከተ የሚሰጠው ማብራሪያ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናት ፍላጎት እንዲያድርባቸው አድርጓል። እነዚህ ነጥቦች ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች ትኩረት የሚስቡት ለምንድን ነው? እንዲህ ያሉ ወሳኝ ጉዳዮችን በተመለከተ አስተማማኝ መረጃ ሊሰጥ የሚችለው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ስለሆነ ነው።—መዝሙር 119:130
5. (ሀ) ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ እንዳያምኑ የሚያደርጓቸው ምክንያቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? (ለ) እንዲህ ያሉ ሰዎችን ልንረዳቸው የምንችለው እንዴት ነው?
ሚክያስ 3:11, 12፤ ማቴዎስ 15:7-9፤ ያዕቆብ 4:4
5 ይሁን እንጂ ሰዎች ፈጽሞ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደማያምኑ ቢነግሩንስ? ውይይታችን በዚሁ ማቆም ይኖርበታል? የሚቀርቡላቸውን አሳማኝ መረጃዎች ለመቀበል ፈቃደኞች እስከሆኑ ድረስ ውይይቱ በዚሁ ማቆም የለበትም። እንዲህ ዓይነት አመለካከት ሊያድርባቸው የቻለው መጽሐፍ ቅዱስን የሕዝበ ክርስትና መጽሐፍ እንደሆነ አድርገው ስለሚያስቡ ሊሆን ይችላል። የሕዝበ ክርስትና ግብዝነትና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዲሁም ሰዎችን በመወትወት ገንዘብ ለመሰብሰብ የምታደርገው ጥረት ለመጽሐፍ ቅዱስ አሉታዊ አመለካከት እንዲያድርባቸው አድርጎ ሊሆን ይችላል። ለመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያለ አመለካከት ሊያድርባቸው የቻለው በዚህ ምክንያት እንደሆነና እንዳልሆነ መጠየቁ ጥሩ ሊሆን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ ሕዝበ ክርስትና የዓለምን መንገድ የምትከተል በመሆኗ እንደሚያወግዛት እንዲሁም በሕዝበ ክርስትናና በእውነተኛ ክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ እንደሚያስቀምጥ ሲረዱ የማወቅ ፍላጎታቸው ሊቀሰቀስ ይችላል።—6. (ሀ) መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል መሆኑን እንድታምን ያደረገህ ምንድን ነው? (ለ) ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል መሆኑን እንዲገነዘቡ ለመርዳት ምን ሌሎች አሳማኝ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል?
6 ለሌሎች ሰዎች ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ መጽሐፍ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን በማቅረብ በቀጥታ ማወያየት የተሻለ ሊሆን ይችላል። አንተ ራስህ መጽሐፍ ቅዱስ የይሖዋ አምላክ ቃል ነው ብለህ እንድታምን ያደረገህ ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስን ያስጻፈው ማን እንደሆነ የሚገልጹት በራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ሐሳቦች ናቸው? ወይስ መጽሐፍ ቅዱስ ወደፊት የሚሆነውን የሚናገሩ ብዙ ትንቢቶች የያዘ በመሆኑና እነዚህ ትንቢቶች ከሰው በላይ ከሆነ ምንጭ የተገኙ መሆን አለባቸው ብለህ ስለምታስብ ነው? (2 ጴጥሮስ 1:20, 21) መጽሐፉ 1,600 ዓመታት በፈጀ ዘመን ውስጥ 40 በሚያክሉ ሰዎች የተጻፈ ቢሆንም በውስጡ ያሉት ሐሳቦች በሚያስደንቅ ሁኔታ እርስ በርሳቸው የሚስማሙ መሆናቸው ነው? ወይስ በዚያ ዘመን ከተጻፉት ጽሑፎች በተለየ ሁኔታ ከሳይንስ ጋር የማይጋጩ ሐሳቦችን የያዘ መሆኑ ነው? ወይስ ጸሐፊዎቹ ጉድለታቸውን ሳይደብቁ በግልጽ መናገራቸው አሊያም መጽሐፉን ለማጥፋት ብዙ ሙከራ ቢደረግም እስከ ዛሬ ድረስ ተጠብቆ መቆየቱ ነው? አንተን ያሳመነህ ምንም ይሁን ምን ሌሎችን ለመርዳት ልትጠቀምበት ትችላለህ። *
የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን
7, 8. (ሀ) ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በተያያዘ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? (ለ) መጽሐፍ ቅዱስን በግላችን ከማንበብ በተጨማሪ ምን ማድረግ ያስፈልገናል? (ሐ) አንተ የይሖዋን ዓላማዎች መረዳት የቻልከው እንዴት ነው?
7 ሌሎች በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲያምኑ ከመርዳት በተጨማሪ እኛ ራሳችን ጊዜ መድበን ዘወትር ልናነበው ይገባል። አንተ ይህን እያደረግክ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ እስከ ዛሬ ከተጻፉት መጻሕፍት ሁሉ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነ መጽሐፍ ነው። እንዲህ ሲባል ግን መጽሐፍ ቅዱስን በግላችን የምናነብ ከሆነ ሌላ ምንም ነገር አያስፈልገንም ማለት አይደለም። ቅዱሳን ጽሑፎች ራስን ማግለል አደገኛ እንደሆነ ይናገራሉ። ሁሉንም ነገር በግል ምርምር በማድረግ ልንደርስበት እንደምንችል አድርገን ማሰብ የለብንም። ሚዛናዊ አመለካከት ያለን ክርስቲያኖች መሆን እንድንችል የግል ጥናት ማድረግ ብቻ ሳይሆን የአምላክ ሕዝቦች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች ላይ አዘውትረን መገኘትም ያስፈልገናል።—ምሳሌ 18:1፤ ዕብራውያን 10:24, 25
8 ከዚህ ጋር በተያያዘ መጽሐፍ ቅዱስ የኢሳይያስን ትንቢት ያነብ ስለነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ ባለ ሥልጣን ይገልጻል። ክርስቲያኑ ወንጌላዊ ፊልጶስ ይህን ሰው “ለመሆኑ፣ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?” ብሎ እንዲጠይቀው አንድ መልአክ አዘዘው። ኢትዮጵያዊውም “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት አድርጌ አስተውላለሁ” ሲል በትሕትና መለሰ። ያነበው የነበረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንዲያብራራለት ፊልጶስን ለመነው። ፊልጶስ ቅዱሳን ጽሑፎችን በተመለከተ የራሱን አስተያየት የሚሰጥ በግሉ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነብ ሰው አልነበረም። ከሚታየው የሐዋርያት ሥራ 6:5, 6፤ 8:5, 26-35) በተመሳሳይ ዛሬም ማንም ሰው በራሱ ጥረት ብቻ የይሖዋን ዓላማዎች በትክክል መረዳት አይችልም። ሁላችንም ይሖዋ በሚታየው ድርጅቱ አማካኝነት የሚሰጠው ፍቅራዊ እገዛ ያስፈልገናል።
የአምላክ ድርጅት ጋር የቅርብ ግንኙነት ነበረው። በመሆኑም ይሖዋ በዚህ ድርጅት አማካኝነት የሚሰጠውን ትምህርት በመጠቀም ኢትዮጵያዊውን ሰው ሊረዳው ችሏል። (9. ሁላችንም ምን ዓይነት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም ቢኖረን ጠቃሚ ነው?
9 የይሖዋ ድርጅት መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እንድንችል እኛን ለማገዝ ሲል በተለያዩ ጽሑፎች አማካኝነት ግሩም የሆኑ ቅዱስ ጽሑፋዊ ትምህርቶች ያዘጋጅልናል። ከዚህም በተጨማሪ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች በሙሉ ከሚካሄደው የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ጋር በተያያዘ የሚጠና ቋሚ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም አለ። ቅዱሳን ጽሑፎችን በግለሰብ ደረጃ በመመርመር ብዙ ጥቅም ማግኘት ይቻላል። (መዝሙር 1:1-3፤ 19:7, 8) መጽሐፍ ቅዱስን ዘወትር ለማንበብ ልዩ ጥረት አድርግ። እያንዳንዱን ነገር በተሟላ ሁኔታ መረዳት ባትችልም እንኳ ስለ ቅዱሳን ጽሑፎች አጠቃላይ ግንዛቤ ማግኘትህ ትልቅ ጥቅም አለው። ለምሳሌ ያህል በቀን አራት ወይም አምስት ገጽ ብታነብ መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ ዓመት ውስጥ ከዳር እስከ ዳር አንብበህ መጨረስ ትችላለህ።
10. (ሀ) መጽሐፍ ቅዱስን የምታነበው መቼ መቼ ነው? (ለ) መጽሐፍ ቅዱስን በምታነብበት ጊዜ እነማንም አብረውህ እንዲያነቡ ማድረግ ይኖርብሃል? ዘወትር ማንበብ አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው?
10 መጽሐፍ ቅዱስን መቼ መቼ ማንበብ ትችላለህ? መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ በቀን ውስጥ 10 ወይም 15 ደቂቃ ብትመድብ እንኳ በእጅጉ ትጠቀማለህ። እንዲህ ማድረግ ካልቻልክ ቢያንስ ቢያንስ በየሳምንቱ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ የምትችልባቸውን ቋሚ ጊዜያት በመመደብ ፕሮግራምህን ለማክበር ጥረት አድርግ። ያገባህ ከሆንክ ደግሞ ከባለቤትህ ጋር አንድ ላይ በመሆን አንዳችሁ ለሌላው ማንበብ ትችላላችሁ። ማንበብ የሚችሉ ልጆች ካሉህ ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በየተራ እንዲያነቡ ማድረግ ትችላለህ። በሕይወት ዘመናችን ሙሉ ምግብ እንደምንበላ ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብም የዕድሜ ልክ ልማዳችን መሆን አለበት። እንደሚታወቀው አንድ ሰው ጥሩ የአመጋገብ ልማድ ከሌለው ጤንነቱ ይቃወሳል። በተመሳሳይም መንፈሳዊ ጤንነታችን ብሎም ዘላለማዊ ሕይወታችን የተመካው ‘ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣውን ቃል ሁሉ’ አዘውትረን በመመገባችን ላይ ነው።—ማቴዎስ 4:4
ግባችን
11. መጽሐፍ ቅዱስ የምናነብበት ዓላማ ምን መሆን ይኖርበታል?
11 መጽሐፍ ቅዱስን የምናነብበት ዓላማ ምን መሆን ይኖርበታል? ግባችን እንዲሁ የተወሰኑ ገጾችን አንብቦ መጨረስ ብቻ አይደለም። ዋናው ዓላማችን አምላክን ይበልጥ በማወቅ ለእሱ ያለን ፍቅር እንዲጨምር ማድረግና እሱን ተቀባይነት ባለው መንገድ ማምለክ ነው። (ዮሐንስ 5:39-42) “እግዚአብሔር ሆይ፤ አካሄድህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝ” ሲል የተናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል።—መዝሙር 25:4
12. (ሀ) “ትክክለኛ ዕውቀት” ማግኘት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? አንድ ሰው ይህን እውቀት እንዲያገኝ በሚያነብበት ጊዜ ምን ጥረት ማድረግ ሊያስፈልገው ይችላል? (ለ) መጽሐፍ ቅዱስን ከየትኞቹ አራት አቅጣጫዎች አንጻር ማንበብ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል? (ገጽ 30 ላይ የሚገኘውን ሣጥን ተመልከት።) (ሐ) በዚህ አንቀጽ ውስጥ የቀረቡትን ጥያቄዎች በምትመልስበት ጊዜ እነዚህን ነጥቦች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል በምሳሌ አስረዳ። ምዕራፋቸውና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱትን ጥቅሶች አውጥተህ አንብብ።
12 ይሖዋ ሲያስተምረን “ትክክለኛ ዕውቀት” የመቅሰም ልባዊ ፍላጎት ሊኖረን ይገባል። ይህን እውቀት ካልቀሰምን የአምላክን ቃል በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ማድረግም ሆነ ቃሉን ለሌሎች በትክክል ማስረዳት እንዴት እንችላለን? (ቈላስይስ 3:10 NW፤ 2 ጢሞቴዎስ 2:15) ትክክለኛ እውቀት ለመቅሰም በጥሞና ማንበብ የሚያስፈልገን ከመሆኑም በላይ በቀላሉ ለመረዳት የሚያስቸግር የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሲያጋጥመን መልእክቱን ለመረዳት ደጋግመን ማንበብ ሊኖርብን ይችላል። በተጨማሪም ትምህርቱን ከተለያዩ አቅጣጫዎች በመመልከት ባነበብነው ሐሳብ ላይ በሚገባ ማሰላሰላችን በእጅጉ ይጠቅመናል። የምናነበውን ሐሳብ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ለማጤን የሚያስችሉ አራት ነጥቦች ገጽ 30 ላይ ቀርበውልናል። አብዛኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ከእነዚህ ነጥቦች በአንዱ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑት ነጥቦች ተጠቅሞ መመርመር ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። በቀጣዮቹ ገጾች ላይ የሰፈሩትን ጥያቄዎች በምትመልስበት ጊዜ ይህን ማድረጉ ምን ያህል ተግባራዊ እንደሆነ ትመለከታለህ።
መዝሙር 139:13, 14 ላይ ይሖዋ በማኅፀን ውስጥ ላለ ፅንስ ያለውን አሳቢነት የሚገልጽ ሐሳብ እናገኛለን:- “በእናቴም ማኅፀን ውስጥ አበጃጅተህ ሠራኸኝ። ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፤ ነፍሴም ይህን በውል ተረድታለች።” የይሖዋ የፍጥረት ሥራዎች ምንኛ ድንቅ ናቸው! ሰዎች የተፈጠሩበት መንገድ ይሖዋ ለእኛ ያለውን ታላቅ ፍቅር ያሳያል።
(1) ብዙውን ጊዜ የምታነበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይሖዋ ምን ዓይነት አምላክ እንደሆነ የሚያስተላልፈው መልእክት ይኖራል። ለምሳሌ ያህል በበዮሐንስ 14:9, 10 ላይ ከተገለጸው ሐሳብ አንጻር ኢየሱስ ከሌሎች ሰዎች ጋር ስላደረገው ግንኙነት የሚገልጽ ዘገባ ስናነብ በተዘዋዋሪ መንገድ ይሖዋ ራሱ የሚያደርገውን ነገር እንማራለን። ይህን በአእምሯችን ይዘን በሉቃስ 5:12, 13 እንዲሁም በሉቃስ 7:11-15 ላይ የሰፈሩትን ዘገባዎች ስናነብ ስለ ይሖዋ ምን ልንገነዘብ እንችላለን?
(2) የምታነበው ዘገባ አስቀድሞ በተነገረለት ዘር ይኸውም በኢየሱስ ክርስቶስ በሚመራው መንግሥት አማካኝነት የይሖዋ ሉዓላዊነት እንደሚረጋገጥና ስሙ እንደሚቀደስ ከሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጥ ጋር ምን ዝምድና እንዳለው አስብ።
ሕዝቅኤልና ዳንኤል የመጽሐፍ ቅዱስን ጭብጥ ጎላ አድርገው የገለጹት እንዴት ነው? (ሕዝቅኤል 38:21-23፤ ዳንኤል 2:44፤ 4:17፤ 7:9-14)
መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ አስቀድሞ የተነገረለት ዘር መሆኑን ለይቶ የሚገልጸው እንዴት ነው? (ገላትያ 3:16)
የራእይ መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጥ የሆነውን የአምላክን መንግሥት በተመለከተ የተሰጡት ተስፋዎች ፍጻሜያቸውን የሚያገኙበትን ሁኔታ የሚገልጸው እንዴት ነው? (ራእይ 11:15፤ 12:7-10፤ 17:16-18፤ 19:11-16፤ 20:1-3፤ 21:1-5)
(3) የምታነበውን ነገር እንዴት በሥራ ላይ ልታውል እንደምትችል ራስህን ጠይቅ። ለምሳሌ ያህል ከዘፀአት እስከ ዘዳግም ድረስ 1 ቆሮንቶስ 10:11
ባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ እስራኤላውያን ስለፈጸሙት የጾታ ብልግናና ዓመጽ የሚገልጽ ዘገባ እናገኛለን። ይህን ዘገባ ስናነብ እንዲህ ያለው ዝንባሌያቸውና ድርጊታቸው መጥፎ መዘዝ እንዳስከተለባቸው እንማራለን። በመሆኑም የእስራኤላውያንን መጥፎ ምሳሌ ባለመኮረጅ ይሖዋን ለማስደሰት መጣጣር ይኖርብናል። “ይህ ሁሉ ምሳሌ ይሆን ዘንድ በእነርሱ ላይ ደረሰ፤ የዘመናት ፍጻሜ የደረሰብንን እኛን ለማስጠንቀቅም ተጻፈ።”—ቃየን አቤልን እንደገደለው የሚገልጸው ታሪክ ለእኛ ምን ትምህርት አለው? (ዘፍጥረት 4:3-12፤ ዕብራውያን 11:4፤ 1 ዮሐንስ 3:10-15፤ 4:20, 21)
ሰማያዊ ተስፋ ላላቸው ክርስቲያኖች የተሰጠው የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር በምድር ለዘላለም የመኖር ተስፋ ላላቸው ክርስቲያኖችም ይሠራል? (ዘኍልቍ 15:16፤ ዮሐንስ 10:16)
ምንም እንኳ በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ጥሩ አቋም ያለን ብንሆንም የምናውቀውን የመጽሐፍ ቅዱስ ምክርም ቢሆን ይበልጥ በተሟላ መንገድ እንዴት ሥራ ላይ ማዋል እንደምንችል ማሰብ የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? (2 ቆሮንቶስ 13:5፤ 1 ተሰሎንቄ 4:1)
(4) የምታነበውን ነገር ሌሎችን ለመርዳት እንዴት ልትጠቀምበት እንደምትችል አስብ። ሁሉም ሰዎች የጤና ጉዳይ በጣም ስለሚያሳስባቸው ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ በሚሆንበት ጊዜ በስፋት የሚፈጽመውን ነገር ለማሳየት ሲል ስላከናወናቸው ድርጊቶች የሚገልጹ ዘገባዎችን ልናነብላቸው እንችላለን:- “ቊጥሩ ብዙ የሆነ ሕዝብም አንካሶችን፣ ዐይነ ስውሮችን፣ ሽባዎችን፣ ዲዳዎችን እንዲሁም ሌሎች ብዙዎችን ሕመምተኞች ይዘው ወደ እርሱ [አመጡ] . . . እርሱም ፈወሳቸው።”—ስለ ኢያኢሮስ ሴት ልጅ ትንሣኤ የሚገልጸውን ታሪክ በመጠቀም እነማንን መርዳት ይቻላል? (ሉቃስ 8:41, 42, 49-56)
13. ከይሖዋ ድርጅት ጋር ሆነን ያለማቋረጥ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበባችንና ማጥናታችን ምን ውጤት ሊያስገኝልን ይችላል?
13 ከላይ የተጠቀሱትን አራት ነጥቦች በአእምሯችን ይዘን መጽሐፍ ቅዱስን የምናነብ ከሆነ በእጅጉ እንጠቀማለን! እውነቱን ለመናገር መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ቀላል አይደለም። ሆኖም ቅዱሳን ጽሑፎችን ስናነብ በመንፈሳዊ እያደግን ስለምንሄድ ዘላቂ ጥቅም ያስገኝልናል። መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረን ማንበባችን አፍቃሪ ከሆነው አባታችን ከይሖዋና ከክርስቲያን ወንድሞቻችን ጋር ይበልጥ እንድንቀራረብ ያደርገናል። ‘የሕይወትን ቃል አጥብቀን እንድንይዝ’ የተሰጠንን ምክር እንድንከተልም ይረዳናል።—ፊልጵስዩስ 2:16 NW
[የግርጌ ማስታወሻ]
^ አን.6 መጽሐፍ ቅዱስ ልንመረምረው የሚገባ መጽሐፍ ነው የምንልበትን ምክንያት በተመለከተ ማብራሪያ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለውን ብሮሹር ተመልከት።
የክለሳ ውይይት
• መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈውና እስከ ዘመናችን ድረስ ተጠብቆ የቆየው ለምንድን ነው?
• ሌሎች ለመጽሐፍ ቅዱስ ከፍ ያለ ግምት እንዲኖራቸው ልንረዳቸው የምንችለው እንዴት ነው?
• መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትሮ ማንበብ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስን ከየትኞቹ አራት አቅጣጫዎች አንጻር ማንበብ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል?
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 30 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]
መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ የሚከተሉትን ነጥቦች አስብባቸው
ስለ ይሖዋ ማንነት ምን መልእክት ያስተላልፋል?
ከጠቅላላው የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጥ ጋር ምን ዝምድና አለው?
ሕይወቴን እንዴት ሊነካው ይገባል?
ሌሎችን ለመርዳት እንዴት ልጠቀምበት እችላለሁ?