ክፍል 3
ኢየሱስ በገሊላ ያከናወነው ታላቅ አገልግሎት
‘ኢየሱስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርቧል” እያለ ይሰብክ ጀመር።’—ማቴዎስ 4:17
በዚህ ክፍል ውስጥ
ምዕራፍ 23
ኢየሱስ በቅፍርናሆም ታላላቅ ሥራዎችን አከናወነ
ኢየሱስ አጋንንትን ሲያስወጣ የአምላክ ልጅ መሆኑን ለሰዎች እንዳይናገሩ ይከለክላቸው ነበር። ለምን?
ምዕራፍ 25
በሥጋ ደዌ የተያዘን ሰው በርኅራኄ ፈወሰ
ኢየሱስ ያደረገው ቀላል የሚመስል ሆኖም ትልቅ ትርጉም ያለው ነገር ለሚፈውሳቸው ሰዎች ከልብ እንደሚያስብ ያሳያል።
ምዕራፍ 30
ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ነው
አይሁዳውያን ኢየሱስ ራሱን ከይሖዋ ጋር እኩል እንዳደረገ ቢሰማቸውም ኢየሱስ፣ አምላክ ከእሱ እንደሚበልጥ በግልጽ ተናግሯል።
ምዕራፍ 40
ይቅርታ ስለ ማግኘት የተሰጠ ትምህርት
ኢየሱስ፣ ምናልባት ዝሙት አዳሪ ለሆነችው ሴት ኃጢአቷ ይቅር እንደተባለ ሲነግራት የአምላክን ሕግ መጣስ ስህተት እንዳልሆነ መግለጹ ነው?
ምዕራፍ 48
ተአምራት ቢፈጽምም በናዝሬት እንኳ ተቀባይነት አላገኘም
የናዝሬት ሰዎች ኢየሱስን ያልተቀበሉት በትምህርቱ ወይም በፈጸማቸው ተአምራት የተነሳ ሳይሆን በሌላ ምክንያት ነው።
ምዕራፍ 50
ስደት ቢኖርም ለመስበክ መዘጋጀት
ኢየሱስ፣ ሞትን እንዳይፈሩ ለሐዋርያቱ የነገራቸው ቢሆንም ስደት ሲያጋጥማቸው እንዲሸሹ ያበረታታቸው ለምንድን ነው?
ምዕራፍ 51
በልደት ግብዣ ላይ የተፈጸመ ግድያ
የሰሎሜ ጭፈራ ሄሮድስን በጣም ስላስደሰተው የጠየቀችውን ማንኛውንም ነገር እንደሚሰጣት ቃል ገባላት። ያቀረበችው ጥያቄ ግን ዘግናኝ ነው፤ ምን ብላ ይሆን?
ምዕራፍ 61
ኢየሱስ ጋኔን የያዘውን ልጅ ፈወሰ
ጋኔን የያዘውን ልጅ መፈወስ ያልተቻለው በእምነት ማነስ ምክንያት እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ። እምነት ያነሰው ማን ነው? ልጁ፣ አባቱ ወይስ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት?
ምዕራፍ 64
ይቅር ባይ የመሆን አስፈላጊነት
ኢየሱስ፣ ይቅር ባይ ያልሆነውን ባሪያ ምሳሌ በመጠቀም አምላክ ሌሎችን ይቅር ለማለት ፈቃደኛ መሆናችንን ምን ያህል አክብዶ እንደሚመለከተው ገልጿል።
ምዕራፍ 65
ወደ ኢየሩሳሌም ሲጓዝ የሰጠው ትምህርት
ኢየሱስ፣ አንድ ሰው የእሱ ተከታይ እንዳይሆን እንቅፋት ሊሆኑበት የሚችሉ አመለካከቶችን ከሦስት ሰዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ገልጿል።