ክፍል አራት
“የስሜንም ቅድስና አስከብራለሁ”—ንጹሕ አምልኮ የሚሰነዘርበትን ጥቃት ተቋቁሞ ያልፋል
ፍሬ ሐሳብ፦ ይሖዋ ሕዝቦቹ ከታላቁ መከራ እንዲተርፉ ያደርጋል
ይሖዋ ሰዎችን ይወዳል፤ ያም ሆኖ ለምናደርጋቸው ነገሮች በኃላፊነት ይጠይቀናል። ይሖዋ እሱን እንደሚያመልኩ እየተናገሩ በምግባራቸው ግን ስለሚክዱት ሰዎች ምን ይሰማዋል? ከታላቁ መከራ ማን እንደሚተርፍ የሚወስነው እንዴት ነው? የፍቅር አምላክ የሆነው ይሖዋ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ክፉ ሰዎችን የሚያጠፋውስ ለምንድን ነው?
በዚህ ክፍል ውስጥ
ምዕራፍ 15
“ምንዝርሽንም አስተውሻለሁ”
በሕዝቅኤልና በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ስለተጠቀሱት ዝሙት አዳሪዎች ወይም አመንዝሮች ከተሰጠው መግለጫ ምን ትምህርት እናገኛለን?
ምዕራፍ 16
‘በግንባራቸው ላይ ምልክት አድርግ’
በሕዝቅኤል ዘመን የነበሩ ታማኝ ሰዎች ከጥፋት እንዲተርፉ ምልክት የተደረገባቸው እንዴት እንደሆነ ማወቃችን ለእኛም ይጠቅመናል።