የሥዕል ማውጫ
በገጽ ቁጥር የተቀመጠ
የፊትና የኋላ ሽፋን ጳውሎስ፣ ጣቢታ፣ ጋልዮስ፣ ሉቃስ፣ የቤተ መቅደስ ጠባቂ ከሐዋርያት ጋር፣ ሰዱቃዊ፣ ጳውሎስ ታጅቦ ወደ ቂሳርያ ሲወሰድ፣ በዘመናችን የድምፅ ማጉያ በተገጠመለት መኪናና በሸክላ ማጫወቻ የስብከቱ ሥራ ሲከናወን።
ገጽ 1 ጳውሎስና ሉቃስ ወደ ሮም በምትሄድ ዕቃ ጫኝ መርከብ ላይ ተሳፍረው፤ ጳውሎስ በሰንሰለት ታስሯል።
ገጽ 2, 3 የበላይ አካል አባላት የሆኑት ወንድም ጆን ባርና ወንድም ቴዎዶር ጃራዝ የዓለም ካርታ እየተመለከቱ።
ገጽ 11 በገሊላ በሚገኝ አንድ ተራራ ላይ ኢየሱስ ለ11 ታማኝ ሐዋርያቱና ለሌሎች ተከታዮቹ ተልእኮ ሲሰጣቸው።
ገጽ 14 ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲያርግ። ሐዋርያቱ ቀና ብለው እየተመለከቱት።
ገጽ 20 በጴንጤቆስጤ ዕለት ደቀ መዛሙርቱ እንግዶችን በገዛ ቋንቋቸው ሲያናግሯቸው።
ገጽ 36 ሐዋርያቱ በንዴት በጦፈው በቀያፋ ፊት ቆመው። የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎች ሐዋርያቱን ለማሰር የሳንሄድሪንን ትእዛዝ በተጠንቀቅ እየተጠባበቁ ነው።
ገጽ 44 ከታች፦ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ አንድ የምሥራቅ ጀርመን ፍርድ ቤት የይሖዋ ምሥክሮችን የአሜሪካ ሰላዮች ናቸው ብሎ በሐሰት ሲፈርድባቸው።—ኖየ በርሊነር ኢሉስትኽየተ የተባለው መጽሔት የጥቅምት 3, 1950 እትም
ገጽ 46 እስጢፋኖስ ተከስሶ ሳንሄድሪን ፊት ቆሟል። ከእስጢፋኖስ ማዶ፣ ሀብታም የሆኑት ሰዱቃውያን፣ ከወዲህ በኩል ደግሞ አክራሪ የሆኑት ፈሪሳውያን አሉ።
ገጽ 54 ጴጥሮስ በአንድ አዲስ ደቀ መዝሙር ላይ እጁን ጭኖ፤ ስምዖን ደግሞ የሳንቲም ከረጢት ይዞ ቆሟል።
ገጽ 75 ጴጥሮስና የጉዞ ጓደኞቹ ወደ ቆርኔሌዎስ ቤት ሲገቡ። ቆርኔሌዎስ የመቶ አለቃ መሆኑን የሚያሳይ ልዩ ካባ በግራ ትከሻው ላይ ጣል አድርጓል።
ገጽ 83 ጴጥሮስ አንድ መልአክ እየመራው ከእስር ቤት ሲወጣ፤ ጴጥሮስ ታስሮ የነበረው በአንቶኒያ ግንብ ሳይሆን አይቀርም።
ገጽ 84 ከታች፦ በ1945 በሞንትሪያል፣ ኩዊቤክ አቅራቢያ የተነሳው የሕዝብ ዓመፅ።—ዊኬንድ ማጋዚን የተባለው መጽሔት የሐምሌ 1956 እትም
ገጽ 91 ጳውሎስንና በርናባስን ከጵስድያዋ አንጾኪያ ሲያስወጧቸው። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም. መባቻ ላይ እንደተገነባ የሚገመተው የከተማዋ አዲሱ የውኃ ማስተላለፊያ ግንብ ከበስተጀርባ ይታያል።
ገጽ 94 ጳውሎስና በርናባስ በልስጥራ ለየት ያለ ክብር እንዳይሰጣቸው ሲከላከሉ። በአደባባይ መሥዋዕት በሚቀርብባቸው ወቅቶች በአብዛኛው አካባቢው እንዲያሸበርቅ ይደረጋል፤ ሙዚቃው ስለሚደምቅ ጫጫታም ይበዛል።
ገጽ 100 ከላይ፦ ሲላስና ይሁዳ በሶርያዋ አንጾኪያ የሚገኘውን ጉባኤ ሲያበረታቱ። (ሥራ 15:30-32) ከታች፦ አንድ የወረዳ የበላይ ተመልካች በኡጋንዳ ለሚገኝ አንድ ጉባኤ ንግግር ሲሰጥ።
ገጽ 107 በኢየሩሳሌም ያለው ጉባኤ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተሰብስቦ።
ገጽ 124 ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በሮማውያን የንግድ መርከብ ተሳፍረው ሲጓዙ። የወደብ መብራት ከርቀት ይታያል።
ገጽ 139 ጳውሎስና ሲላስ በቁጣ ገንፍሎ ከወጣ ሕዝብ ለማምለጥ አንድ ግቢ ውስጥ ሲገቡ።
ገጽ 155 ጋልዮስ የጳውሎስን ከሳሾች ሲያባርራቸው። ለሥልጣኑ የሚመጥን ልብስ ለብሷል፤ ወይን ጠጅ ጥለት ያለው ነጭ የንጉሣውያን ልብስ እንዲሁም ካልኬ የሚባለውን ጫማ አድርጓል።
ገጽ 158 ድሜጥሮስ በኤፌሶን በሚገኝ የብር አንጥረኛ ሱቅ ውስጥ ሠራተኞቹን ሲያናግር። ከብር የተሠሩ የአርጤምስ ቤተ መቅደስ ቅርጾች እንደ ስጦታ ዕቃ ይሸጡ ነበር።
ገጽ 171 ጳውሎስና የጉዞ ጓደኞቹ መርከብ ሲሳፈሩ። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. የተገነባው የታላቁ ወደብ ሐውልት ከበስተጀርባ ይታያል።
ገጽ 180 ከታች፦ በ1940ዎቹ በካናዳ ጽሑፎቻችን በታገዱበት ወቅት አንድ ወጣት የይሖዋ ምሥክር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን በድብቅ ሲያመጣ። (አስመስሎ የተነሳ ፎቶግራፍ።)
ገጽ 182 ጳውሎስ ሽማግሌዎቹ ያቀረቡለትን ጥያቄ ሲቀበል። መዋጮውን ለማድረስ አብረውት የመጡት ሉቃስና ጢሞቴዎስ ከበስተኋላ ተቀምጠዋል።
ገጽ 190 የጳውሎስ እህት ልጅ ቀላውዴዎስ ሉስዮስን ሲያነጋግረው፤ ቦታው ጳውሎስ እንደታሰረበት የሚገመተው የአንቶኒያ ግንብ ነው። ከበስተጀርባ የሄሮድስ ቤተ መቅደስ ይታያል።
ገጽ 206 ጳውሎስ በአንድ የጭነት መርከብ ውስጠኛ ክፍል ሆኖ በጉዞ ለዛሉት መንገደኞች ሲጸልይ።
ገጽ 222 እስረኛው ጳውሎስ ከአንድ የሮም ወታደር ጋር በሰንሰለት ተቆራኝቶ የሮምን ከተማ በከፊል እየተመለከተ።