በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክፍል 4 ክለሳ

ክፍል 4 ክለሳ

ከአስተማሪህ ጋር በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  1. ምሳሌ 13:20ን አንብቡ።

    •   ጓደኞችህን በጥበብ መምረጥህ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

      (ምዕራፍ 48ን ተመልከት።)

  2. መጽሐፍ ቅዱስ ምን ጠቃሚ ምክር ይዟል?

    •   ለባሎች ወይም ለሚስቶች

    •   ለወላጆች ወይም ለልጆች

      (ምዕራፍ 49ን እና 50ን ተመልከት።)

  3. ይሖዋን የሚያስደስተው ምን ዓይነት አነጋገር ነው? የሚያሳዝነውስ ምን ዓይነት አነጋገር ነው?

    (ምዕራፍ 51ን ተመልከት።)

  4. ከአለባበስህና በአጠቃላይ ከውጫዊ ገጽታህ ጋር በተያያዘ ጥሩ ምርጫ ለማድረግ የሚረዱህ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ናቸው?

    (ምዕራፍ 52ን ተመልከት።)

  5. ይሖዋን የሚያስደስት መዝናኛ መምረጥ የምትችለው እንዴት ነው?

    (ምዕራፍ 53ን ተመልከት።)

  6. ማቴዎስ 24:45-47ን አንብቡ።

    •   “ታማኝና ልባም ባሪያ” ማን ነው?

      (ምዕራፍ 54ን ተመልከት።)

  7. ጊዜህን፣ ጉልበትህንና ገንዘብህን ተጠቅመህ ለጉባኤው ድጋፍ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

    (ምዕራፍ 55ን ተመልከት።)

  8. መዝሙር 133:1ን አንብቡ።

    •   ለጉባኤው አንድነት የበኩልህን አስተዋጽኦ ማበርከት የምትችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

      (ምዕራፍ 56ን ተመልከት።)

  9. ከባድ ኃጢአት ከፈጸምን የይሖዋን እርዳታ ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?

    (ምዕራፍ 57ን ተመልከት።)

  10. አንደኛ ዜና መዋዕል 28:9ን እና የግርጌ ማስታወሻውን አንብቡ።

    •   ሌሎች እውነተኛውን አምልኮ በሚቃወሙበት ወይም እውነትን በሚተዉበት ጊዜ ‘ሙሉ በሙሉ ለይሖዋ እንዳደርክ’ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

    •   ለይሖዋ ታማኝ ሆነህ ለመቀጠልና ከሐሰት ሃይማኖት ሙሉ በሙሉ ለመራቅ ልትወስደው የሚገባ እርምጃ ይኖር ይሆን?

      (ምዕራፍ 58ን ተመልከት።)

  11. ለስደት አስቀድመህ መዘጋጀት የምትችለው እንዴት ነው?

    (ምዕራፍ 59ን ተመልከት።)

  12. መንፈሳዊ እድገት ማድረግህን ለመቀጠል ምን ዕቅድ አውጥተሃል?

    (ምዕራፍ 60ን ተመልከት።)