በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ሰርጌ ሉኪን

ግንቦት 21, 2024 | የታደሰው፦ ታኅሣሥ 11, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | ለይሖዋ ስም ጥብቅና መቆም ክብር ነው

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | ለይሖዋ ስም ጥብቅና መቆም ክብር ነው

ታኅሣሥ 11, 2024 በአልታይ ግዛት የሚገኘው የቢስክ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ሰርጌ ሉኪን ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል፤ የአራት ዓመት ከስድስት ወር የገደብ እስራት ተፈርዶበታል። አሁን ወህኒ አይወርድም።

አጭር መግለጫ

ለይሖዋ ያለን ፍቅር ‘ፍርሃትን አውጥቶ እንደሚጥል’ በሚያረጋግጥልን በሰርጌ ምሳሌ ተበረታተናል።​—1 ዮሐንስ 4:18

የክሱ ሂደት

  1. ታኅሣሥ 1, 2022

    የክስ ፋይል ተከፈተበት

  2. ጥር 25, 2023

    መኖሪያ ቤቱና ቢሮው ተፈተሹ። ምርመራ ከተደረገበት በኋላ የጉዞ ክልከላዎች ተጣሉበት

  3. ጥር 25, 2024

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ