በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከጥር 6-12

መዝሙር 127–134

ከጥር 6-12

መዝሙር 134 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ወላጆች—ውድ ውርሻችሁን መንከባከባችሁን ቀጥሉ

(10 ደቂቃ)

ወላጆች ቤተሰባቸውን ለመንከባከብ ይሖዋ እንደሚረዳቸው መተማመን ይችላሉ (መዝ 127:1, 2)

ልጆች ከይሖዋ የተገኙ ውድ ስጦታዎች ናቸው (መዝ 127:3w21.08 5 አን. 9)

ለልጆቻችሁ ሥልጠና ስትሰጡ እያንዳንዱ ልጅ የሚያስፈልገውን ነገር ከግምት አስገቡ (መዝ 127:4w19.12 27 አን. 20)

ይሖዋ ወላጆች በእሱ በመታመን ልጆቻቸውን ለመንከባከብ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ሲያደርጉ ይደሰታል

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 128:3—መዝሙራዊው ወንዶች ልጆችን ከወይራ ዛፍ ቡቃያዎች ጋር ያመሳሰላቸው ለምንድን ነው? (w00 5/15 27 አን. 3-5)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 3)

5. ውይይት መጀመር

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ግለሰቡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የሚጋጭ ሐሳብ ተናግሯል። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 4)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 16 ነጥብ 4-5። በሚቀጥለው ሳምንት አንተ ወደ ሌላ አካባቢ ብትሄድም ተማሪው ጥናቱን እንዲያጠና ስላደረግከው ዝግጅት ተወያዩ። (lmd ምዕራፍ 10 ነጥብ 4)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 13

7. ወላጆች—ይህን ውጤታማ የማስተማሪያ መሣሪያ እየተጠቀማችሁበት ነው?

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ወላጆች ልጆቻቸውን ስለ ይሖዋ እንዲያስተምሩ ለመርዳት የይሖዋ ድርጅት ስፍር ቁጥር የሌላቸውን የሕትመት ውጤቶች አዘጋጅቷል። ያም ቢሆን፣ ወላጆች ሊጠቀሙባቸው ከሚችሏቸው በጣም ውጤታማ መሣሪያዎች አንዱ መልካም ምሳሌነታቸው ነው።—ዘዳ 6:5-9

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለማስተማር ይህን ውጤታማ መሣሪያ ተጠቅሞበታል።

ዮሐንስ 13:13-15ን አንብብ ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ኢየሱስ ምሳሌ በመሆን ማስተማሩ ውጤታማ የሆነው ለምን ይመስላችኋል?

ወላጆች፣ ድርጊታችሁ ለልጆቻችሁ በቃል ለምታስተምሩት ትምህርት ማጠናከሪያ ይሆናል። በተጨማሪም መልካም ምሳሌነታችሁ ልጆቻችሁ ለምታስተምሯቸው ትምህርት አክብሮት እንዲኖራቸው ያደርጋል፤ እንዲያዳምጧችሁም ያነሳሳቸዋል።

ምሳሌ በመሆን ልጆቻችንን አስተምረናል የተባለውን ቪዲዮ አጫውት ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • ወንድም ጋርሲያ እና ባለቤቱ ለልጆቻቸው የትኞቹን አስፈላጊ ትምህርቶች አስተምረዋል?

  • ይህ ቪዲዮ ለልጆቻችሁ መልካም ምሳሌ መሆናችሁን ለመቀጠል የሚያነሳሳችሁ እንዴት ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 73 እና ጸሎት