ፈገግታ
አውርድ፦
1. ለከፋው፣ ሆድ ለባሰው ሰው
ምን ቃል ነው ’ሚፈውሰው?
የተባ አንደበት ነው ወይ
ልቡን የሚያርሰው?
አዎ፣ ደግነት መልካም ነው፣
ለቸገረው መስጠቱ፤
ቁልፉ ግን ሚስጥሩ፣
ከፍትፍቱ ፊቱ!
(አዝማች)
ፈገግታ፣ ለራበው ያጠግባል፤
ፈገግታ፣ ቋንቋ ነው ያግባባል።
ሳይነበብ ጥቅሱ፣ ቃልም ሳይወጣ
ይናገራል ደስ የሚል ፈገግታ!
2. ምስኪኑ ሲንገላታ፣ አንገት ሲያስደፋው ኑሮ፣
አይዞህ፣ ቀና በል የሚለው፣ ሰው የታለ ዘንድሮ?
ይ’ም ቀን ያልፋል ማን ይበለው? ማን ያጽናናው በተስፋው?
በመንገዱ፣ በጎዳናው እንስበክ ለተገፋው።
(አዝማች)
ፈገግታ፣ ለራበው ያጠግባል፤
ፈገግታ፣ ቋንቋ ነው ያግባባል።
ሳይነበብ ጥቅሱ፣ ቃልም ሳይወጣ
ይናገራል ደስ የሚል ፈገግታ!
3. አንዳንድ ቀን ግን አለ ውሎው የሚያስከፋ፣
ደክመን፣ ብዙ ሞክረን ሰሚ ጆሮ ሲጠፋ፤
ተስፋ ቆርጠን ግን አንቀርም፤ እዚያው ነን በማግስቱ።
ፈገግታ ልብ ያሸንፋል ከፍትፍቱ ፊቱ!
(አዝማች)
ፈገግታ፣ ለራበው ያጠግባል፤
ፈገግታ፣ ቋንቋ ነው ያግባባል።
ሳይነበብ ጥቅሱ፣ ቃልም ሳይወጣ
ይናገራል ደስ የሚል ፈገግታ!