በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 8

የጌታ ራት

የጌታ ራት

(ማቴዎስ 26:26-30)

1. ይሖዋ የሰማዩ አባት፣

የዛሬዋ ቀን ቅዱስ ናት!

በኒሳን አሥራ ’ራት ተገለጠ ክብርህ፤

ፍቅርህ፣ ፍትሕ፣ ጥበብ፣ ኃይልህ።

የፋሲካውም በግ ተበላ፤

እስራኤልም ነፃ ወጣ።

ጌታችን ደሙን አፈሰሰ በዚህ ’ለት፤

ፈጸመ የፋሲካን ትንቢት።

2. በፊትህ ቀርበናል በዚህ ቀን፣

ለማክበር ቅዱስ ስምህን፤

ላሳየኸን ፍቅር በመስጠት ልጅህን፣

አንተን ከልብ ለማመስገን።

ዘወትር ይህን ቀን እናስብ፤

ምንጊዜም ይደር በኛ ልብ።

እንኑር ሁልጊዜ በክርስቶስ ትም’ርት፤

ለማግኘት የዘላለም ሕይወት።

(በተጨማሪም ሉቃስ 22:14-20⁠ን እና 1 ቆሮ. 11:23-26⁠ን ተመልከት።)