መዝሙር 96
የሚገባቸውን ሰዎች ፈልጉ
1. እንዴት መስበክ እንዳለብን ነግሮናል፤
ጌታ መመሪያ ሰጥቶናል፦
‘‘በሁሉም ስፍራ ፈልጉ ቅኖችን፤
በመንፈሳዊ ’ሚራቡትን።
ለቤተሰቡ ሰላምን ተመኙ፤
’ሚገባው ከሆነ ይድረሰው።
እንቢ ካሉ ግን የ’ግራቹን አቧራ
አራግፋችሁ ሂዱ፣ ተዉአቸው።’
2. ’ሚቀበላችሁ ጌታን ይቀበላል።
ልቡ ይከፈትለታል።
ጥሩ የልብ ዝንባሌ ስላለው፣
እሱም ማገልገል ይጀምራል።
‘ምን እንላለን?’ ብላችሁ አትስጉ፤
ይረዳችኋል አምላካችሁ።
ንግግራችሁ ቢሆን ለዛ ያለው፣
ይሳባል ቅንና ትሑት ሰው።