በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 27

ከይሖዋ ጎን ቁም!

ከይሖዋ ጎን ቁም!

(ዘፀአት 32:26)

1. ግራ ገብቶን ነበር እጅግ አዝነን፣

በሐሰት ትምህርቶች ተተብትበን፤

ስለ አምላክ መንግሥት ስንሰማ ግን፣

ፈነደቀ ልባችን።

(አዝማች)

ከይሖዋ ጎን ቁም፤

ተደሰት በሱም።

አይጥልህም አምላክ፤

ሂድ በሱ ብርሃን።

የሰላም ምሥራች፣

አብስር ለሰዎች።

ይስፋፋ መንግሥቱ፤

ይታይ እድገቱ።

2. እናገለግላለን አምላክን፤

እውነትን በደስታ እንሰብካለን፤

እንርዳቸው ወንድሞቻችንን፣

እንዲያወድሱ ስሙን።

(አዝማች)

ከይሖዋ ጎን ቁም፤

ተደሰት በሱም።

አይጥልህም አምላክ፤

ሂድ በሱ ብርሃን።

የሰላም ምሥራች፣

አብስር ለሰዎች።

ይስፋፋ መንግሥቱ፤

ይታይ እድገቱ።

3. አንፈራም የሰይጣንን ጥቃት።

በአምላክ ላይ አለን ሙሉ እምነት።

ብዙ ቢሆኑም ጠላቶቻችን፣

ይሖዋ ነው ኃይላችን።

(አዝማች)

ከይሖዋ ጎን ቁም፤

ተደሰት በሱም።

አይጥልህም አምላክ፤

ሂድ በሱ ብርሃን።

የሰላም ምሥራች፣

አብስር ለሰዎች።

ይስፋፋ መንግሥቱ፤

ይታይ እድገቱ።

(በተጨማሪም መዝ. 94:14⁠ን፣ ምሳሌ 3:5, 6⁠ን እና ዕብ. 13:5⁠ን ተመልከት።)