በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 84

“እፈልጋለሁ”

“እፈልጋለሁ”

(ሉቃስ 5:13)

1. ያምላክ ልጅ ፍቅር አሳየን፤

ትቶ በመምጣት ሰማይን።

ራሱን ዝቅ አድርጎ ከሰው ጋር ኖረ፤

እውነትንም አስተማረ።

አጽናና የሰው ልጆችን፤

ፈወሰ የታመሙትን።

ተል’ኮውን ተወጣ በደስታ፤

“’ፈልጋለሁ” አለ ጌታ።

2. አምላክ ረዳት አዘጋጅቷል፤

ታማኙን ባሪያ ሰጥቶናል።

በደስታ አብረነው እንሠራለን፤

ለመርዳት ትሑት ሰዎችን።

ከልብ የሚወዷቸውን

ስለሚያውቁ በቀላሉ፣

አጋር፣ ወላጅ ያጡ ሲቸገሩ

‘መርዳት ’ፈልጋለሁ’ በሉ።

(በተጨማሪም ዮሐ. 18:37⁠ን፣ ኤፌ. 3:19⁠ን እና ፊልጵ. 2:7⁠ን ተመልከት።)