በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 34

እንደ ስማችን መኖር

እንደ ስማችን መኖር

(ኢሳይያስ 43:10-12)

1. ልዑል ይሖዋ፣ ዘላለማዊ ነህ፤

ወደር የለው ፍቅርህ፣ ፍትሕ፣ ኃይልህ።

አንተ ነህ ምንጩ የጥበብ፣ የእውነት፤

ሉዓላዊ፣ ሁሉን ቻይ ጌታ ነህ።

በጣም ያስደስታል አንተን ማገልገል፤

እውነትንም ለሰዎች መናገር።

(አዝማች)

ክብር ነው ያንተ ምሥክሮች መሆን፤

እርዳን እንደ ስማችን ለመኖር!

2. በአገልግሎት አብረን ስንካፈል፣

ፍቅርና ሰላም ይኖረናል።

ስለ ክብርህ ለሰዎች ስንናገር፣

አንተን ስናወድስ ደስ ይለናል።

አባታችን ሆይ፣ በስምህ ተጠራን፤

ዝናህን ለማወጅ መብት አገኘን።

(አዝማች)

ክብር ነው ያንተ ምሥክሮች መሆን፤

እርዳን እንደ ስማችን ለመኖር!

(በተጨማሪም ዘዳ. 32:4⁠ን፣ መዝ. 43:3⁠ን እና ዳን. 2:20, 21⁠ን ተመልከት።)