በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 10

“እነሆኝ! እኔን ላከኝ!”

“እነሆኝ! እኔን ላከኝ!”

(ኢሳይያስ 6:8)

1. አምላክ ዛሬ ስሙ ጠፍቷል፤

ጨካኝ ተደርጎ ተቆጥሯል።

‘ደካማ ነው’ ብለውታል፤

ሞኝም “አምላክ የለም” ይላል።

ማን ነው ጥብቅና ’ሚቆመው?

አምላክን የሚያወድሰው?

“ጌታ ’ነሆኝ! እኔን ላከኝ፤

ለመናገር ድፍረት አለኝ።

(አዝማች)

ከዚህ በላይ ምን ክብር ሊገኝ፤

እነሆኝ! እኔን ላከኝ!”

2. አይፈሩም ሲገዳደሩት፣

‘እርምጃ አይወስድም’ ሲሉት።

ጣዖት ሠርተው አመለኩ፤

ቦታውን በቄሳር ተኩ።

ማን ሄዶ ያስጠንቅቃቸው?

“ጥፋት መጣ” ይበላቸው?

“ጌታ ’ነሆኝ! እኔን ላከኝ፤

አሰማለሁ ውዳሴህን።

(አዝማች)

ከዚህ በላይ ምን ክብር ሊገኝ፤

እነሆኝ! እኔን ላከኝ!”

3. ዓለም በክፋት ተሞልቷል፤

ገሮች አዝነው አልቅሰዋል።

ሰላም ’ሚሰጠውን እውነት፣

ያስፈልጋቸዋል ማግኘት።

ማን ነው ሄዶ ’ሚያጽናናቸው?

መንገዱን የሚያሳያቸው?

“ጌታ ’ነሆኝ! እኔን ላከኝ፤

ለማስተማር ት’ግሥት አለኝ።

(አዝማች)

ከዚህ በላይ ምን ክብር ሊገኝ፤

እነሆኝ! እኔን ላከኝ!”

(በተጨማሪም መዝ. 10:4⁠ን እና ሕዝ. 9:4⁠ን ተመልከት።)