በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 90

ሽበት ያለው ውበት

ሽበት ያለው ውበት

(ምሳሌ 16:31)

1. አረጋውያን አሉ፣ በኛ መካከል፤

የጸኑ ለዘመናት፣ ዛሬም ቆመዋል።

አጋርን ሲያጡ በሞት፣

ሲደክም ጉልበት፣

አባት ሆይ፣ ይታያቸው፤

በ’ምነት ተስፋቸው።

(አዝማች)

የ’ምነት ሩጫቸውን

አባት ሆይ፣ አስታውስ።

ስትላቸው “ጎበዝ!”

ይላቸዋል ደስ።

2. በጽድቅ ያገኙት ሽበት፣

አለው ድንቅ ውበት።

በአምላክ ዘንድ ታማኝ ሰው፣

ምንጊዜም ውብ ነው።

አንዘንጋ ’ነሱም ወጣት እንደነበሩ፣

አቅም ባላቸው ጊዜ ምርጡን የቸሩ።

(አዝማች)

የ’ምነት ሩጫቸውን

አባት ሆይ፣ አስታውስ።

ስትላቸው “ጎበዝ!”

ይላቸዋል ደስ።

(በተጨማሪም ማቴ. 25:21, 23⁠ን፣ መዝ. 71:9, 18⁠ን፣ ምሳሌ 20:29⁠ን፣ ሉቃስ 22:28⁠ን እና 1 ጢሞ. 5:1⁠ን ተመልከት።)