የሚስጥር አጠባበቅ ማስተካከያ

በjw.org ላይ ጥሩ የዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ኩኪዎችንና ሌሎች ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን። አንዳንድ ኩኪዎች ድረ ገጹ እንዲሠራ የግድ ስለሚያስፈልጉ መከልከል አይቻልም። አጠቃቀምህን ለማሻሻል ብቻ የምንጠቀምባቸውን ሌሎች ተጨማሪ ኩኪዎች መፍቀድ ወይም መከልከል ትችላለህ። ይህ መረጃ በፍጹም አይሸጥም ወይም ለንግድ ዓላማ አይውልም። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ገጽ ተመልከት፦ የኩኪዎችንና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ዓለም አቀፍ ፖሊሲ በማንኛውም ጊዜ ምርጫዎችን ማስተካከል ከፈለግክ ይህን ገጽ ተጠቀም፦ የሚስጥር አጠባበቅ ማስተካከያ

በእሳት በጋየ አንድ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ከእሳቱ የተረፈ ዕቃ ሲለቃቅሙ

አምላክ በአንተ ላይ ስለሚደርሰው መከራ ምን ይሰማዋል?

አምላክ በአንተ ላይ ስለሚደርሰው መከራ ምን ይሰማዋል?

አንዳንድ ሰዎች አምላክ በእኛ ላይ የሚደርሰውን መከራ እንደማያይ፣ ቢያይም ግድ እንደማይሰጠው ይሰማቸዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

  • አምላክ የሚደርስብንን መከራ የሚያይ ከመሆኑም ሌላ ግድ ይሰጠዋል

    “ይሖዋ የሰው ልጅ ክፋት በምድር ላይ እንደበዛ . . . ተመለከተ። . . . ልቡም አዘነ።”—ዘፍጥረት 6:5, 6

  • አምላክ መከራን ሁሉ ያስወግዳል

    “ለጥቂት ጊዜ ነው እንጂ ክፉዎች አይኖሩም፤ በቀድሞ ቦታቸው ትፈልጋቸዋለህ፤ እነሱ ግን በዚያ አይገኙም። የዋሆች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤ በብዙ ሰላምም እጅግ ደስ ይላቸዋል።”—መዝሙር 37:10, 11

  • አምላክ ለአንተ የሚመኝልህ ነገር

    “‘ለእናንተ የማስበውን ሐሳብ በሚገባ አውቀዋለሁና’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለእናንተ የማስበው ጥፋትን ሳይሆን ሰላምን እንዲሁም የተሻለ ሕይወትንና ተስፋን ነው። እናንተም ትጠሩኛላችሁ፤ ወደ እኔም ቀርባችሁ ትጸልያላችሁ፤ እኔም እሰማችኋለሁ።’”—ኤርምያስ 29:11, 12

    “ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል።”—ያዕቆብ 4:8