ጥያቄ 13

መጽሐፍ ቅዱስ ሥራን አስመልክቶ ምን ይላል?

 “በሥራው የተካነን ሰው አይተሃል? በነገሥታት ፊት ይቆማል፤ ተራ በሆኑ ሰዎች ፊት አይቆምም።”

ምሳሌ 22:29

 “የሚሰርቅ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ከዚህ ይልቅ ለተቸገረ ሰው የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በእጆቹ መልካም ተግባር እያከናወነ በትጋት ይሥራ።”

ኤፌሶን 4:28

 “ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ተግቶ በሚሠራው ሥራ ሁሉ ደስታ ከማግኘት የተሻለ ነገር የለም። ይህ የአምላክ ስጦታ ነው።”

መክብብ 3:13