የበላይ ተመልካቾች
የበላይ ተመልካቾች ምክንያታዊ በሆነ መጠንም ቢሆን የትኞቹን ብቃቶች ማሟላት አለባቸው?
የጉባኤ የበላይ ተመልካቾች ከሁሉም ክርስቲያኖች በሚጠበቁ በየትኞቹ ብቃቶችም ምሳሌ ሊሆኑ ይገባል?
ማቴ 28:19, 20፤ ገላ 5:22, 23፤ 6:1፤ ኤፌ 5:28፤ 6:4፤ 1ጢሞ 4:15፤ 2ጢሞ 1:14፤ ቲቶ 2:12, 14፤ ዕብ 10:24, 25፤ 1ጴጥ 3:13
የጉባኤ አገልጋዮች ምክንያታዊ በሆነ መጠንም ቢሆን የትኞቹን ብቃቶች ማሟላት አለባቸው?
ወንድሞች የበላይ ተመልካቾች እንዲሆኑ በሚሾሙበት ወቅት የመንፈስ ቅዱስ ሚና ምንድን ነው?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ሥራ 13:2-5፤ 14:23—ተጓዥ የበላይ ተመልካቾቹ ጳውሎስና በርናባስ በየጉባኤው ወንድሞችን ሾመዋል፤ በዛሬው ጊዜ ያሉ የወረዳ የበላይ ተመልካቾችም እንዲሁ ያደርጋሉ፤ ይህን በሚያደርጉበት ወቅት መንፈስ ቅዱስ ለማግኘት ይጸልያሉ እንዲሁም በመንፈስ መሪነት በተጻፉት ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ የተዘረዘሩትን ብቃቶች በጥንቃቄ ያመሣክራሉ
-
ጉባኤው የማን ንብረት ነው? ምን ዋጋስ ተከፍሎበታል?
የበላይ ተመልካቾች አገልጋዮች እንደሆኑ ተደርገው የተገለጹት ለምንድን ነው?
የበላይ ተመልካቾች ምንጊዜም ትሑት መሆን ያለባቸው ለምንድን ነው?
አንድ ክርስቲያን የበላይ ተመልካች ‘ከታማኝና ልባም ባሪያ’ ለሚመጣ መመሪያ ምን አመለካከት ሊኖረው ይገባል?
ሽማግሌዎች ሌሎችን ማስተማር የሚችሉበት ከሁሉ የተሻለ መንገድ ምንድን ነው?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ነህ 5:14-16—አገረ ገዢው ነህምያ ለይሖዋ ካለው ፍርሃትና ጥልቅ አክብሮት የተነሳ በአምላክ ሕዝብ ላይ ያለውን ሥልጣን አላግባብ ለመጠቀም አልፈለገም፤ መብቱ የሆነውን ነገር እንኳ አልጠየቀም
-
ዮሐ 13:12-15—ኢየሱስ ትሕትናን ለተከታዮቹ ያስተማረው ምሳሌ በመሆን ነው
-
አንድ ክርስቲያን እረኛ በጉባኤው ውስጥ ላሉት ሁሉ በግለሰብ ደረጃ ፍቅርና አሳቢነት ማሳየት የሚችለው እንዴት ነው?
ሽማግሌዎች በመንፈሳዊ የታመሙትን የሚያግዙት እንዴት ነው?
ሽማግሌዎች ከማስተማር ጋር በተያያዘ ምን ኃላፊነት አለባቸው?
1ጢሞ 1:3-7፤ 2ጢሞ 2:16-18፤ ቲቶ 1:9
በተጨማሪም 2ቆሮ 11:2-4ን ተመልከት
ሽማግሌዎች የጉባኤውን ሥነ ምግባራዊ ንጽሕና ለመጠበቅ ተግተው መሥራት ያለባቸው ለምንድን ነው?
1ቆሮ 5:1-5, 12, 13፤ ያዕ 3:17፤ ይሁዳ 3, 4፤ ራእይ 2:18, 20
በተጨማሪም 1ጢሞ 5:1, 2, 22ን ተመልከት
ሽማግሌዎች ለሌሎች ምን ሥልጠና ይሰጣሉ?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ማቴ 10:5-20—ኢየሱስ 12 ሐዋርያቱን ለስብከት ከመላኩ በፊት አሠልጥኗቸዋል
-
ሉቃስ 10:1-11—ኢየሱስ 70ዎቹን ደቀ መዛሙርት ለስብከት ከመላኩ በፊት ዝርዝር መመሪያዎች ሰጥቷቸዋል
-
ሽማግሌዎች ያሉባቸውን በርካታ ኃላፊነቶች እንዲወጡ ምን ይረዳቸዋል?
በተጨማሪም ምሳሌ 3:5, 6ን ተመልከት
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
1ነገ 3:9-12—ንጉሥ ሰለሞን የይሖዋን ሕዝብ ለመዳኘት የሚያስችል ጥበብና ማስተዋል እንዲሰጠው ወደ ይሖዋ ጸልዮአል
-
2ዜና 19:4-7—ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በየከተሞቹ ፈራጆችን ሾመ፤ ይህን ታላቅ ኃላፊነት ሲወጡ ይሖዋ አብሯቸው እንደሚሆን ፈራጆቹን አስታወሳቸው
-
ጉባኤው ለታማኝ የበላይ ተመልካቾች ምን አመለካከት ሊኖረው ይገባል?
1ተሰ 5:12, 13፤ 1ጢሞ 5:17፤ ዕብ 13:7, 17
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ሥራ 20:37—የኤፌሶን ክርስቲያኖች ለሐዋርያው ጳውሎስ ፍቅራቸውን ከመግለጽ ወደኋላ አላሉም
-
ሥራ 28:14-16—የሮም ክርስቲያኖች ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ሮም እየመጣ መሆኑን በሰሙ ጊዜ 65 ኪሎ ሜትር በመጓዝ እስከ አፍዩስ የገበያ ስፍራ መጥተው ተቀብለውታል፤ እሱም እነሱን በማየቱ በጣም ተበረታቷል
-